ሐምሌ 17፣ 2016 አዋሽ ባንክ በተጠናቀቀው 2016 በጀት ዓመት 11.6 ቢሊዮን ብር አተረፍኩ አለ።… — Bole Stock Exchange — TG.ME

ሐምሌ 17፣ 2016

አዋሽ ባንክ በተጠናቀቀው 2016 በጀት ዓመት 11.6 ቢሊዮን ብር አተረፍኩ አለ።
#ShegerFM

ትርፉ ከተቀናናሽ ወይም depreciation በፊት መሆኑን የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ ፀሀይ ሽፈራሁ ተናግረዋል ።

የባንኩ ጠቅላላ ገቢ በ27 በመቶ እድገት በማሳየት 36.4 ቢሊዮን ብር ደርሷል ተብሏል።

የተጠናቀቀው የበጀት ዓመት"ምንም እንኳን በአለም አቀፍ እንዲሁም በሀገር አቀፍ ደረጃ የተከሰቱ አስቸጋሪ ሁኔታዎች የባንኩን ዘርፍ ቢፈታተኑትም አዋሽ ባንክ ከዓመት በፊት ነድፎ ተግባራዊ እያደረገ ባለው የአምስት ዓመት እስትራቴጂክ ዕቅዱ በመመራት በበጀት ዓመቱ በሁሉም ዋና ዋና የባንክ ስራ አፈጻፀም መለኪያዎች አጥጋቢ ውጤት አስመዝግቧል ሲሉ አቶ ፀሀይ አስረድተዋል።

የባንኩ ተቀማጭ ገንዘብ 232 ቢሊዮን ብር ደርሷል የተባለ ሲሆን ይህም ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ45.1 ቢሊዮን ብር ወይም በ24 በመቶ ዕድገት አሳይቷል ተብሏል፡፡

ጠቅላላ ተቀማጩን ወደ ብር 19 ቢሊዮን ብር መድረሱም ተነግሯል።

አዋሽ ባንክ በሂሳብ ዓመቱ ለተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች በአጠቃላይ ከ37.6 ቢሊዮን ብር በላይ አዳዲስ ብድሮችን ሰጥቻለሁ ብሏል።

በተጠናቀቀዉ የሂሳብ ዓመት የባንኩ የተከፈለ ካፒታል 20.3 ቢሊዮን ብር በላይ፣ጠቅላላ ሃብቱ ደግሞ 300 ቢሊዮን ብር በላይ ደርሷል ሲሉ ዋና ስራ አሰፈፃሚው ተናግረዋል ።

አዋሽ ባንክ በተጠናቀቀዉ የሂሳብ ዓመት ሁለት ከኢትዮጵያ ምርጥ ባንክ በመባል በግሎባል ፋይናንስ መጋዚን መመረጡን፤ ከዓለም አቀፍ ባንከሮች (International Bankers) ደግሞ ከኢትዮጵያ የዓመቱ ምርጥ ኮሜርሻል ባንክ በመባል ዕውቅና ማግኘቱን አስታወሷል።
👍2
July 24, 2024 960 2