ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ1.2 ቢልየን ብር በላይ አተረፈ። ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ… — Bole Stock Exchange — TG.ME

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ1.2 ቢልየን ብር በላይ አተረፈ።

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ሁሉን አቀፍ በሆነ የዕድገትና የስኬት ጉዞ ላይ የሚገኝ ሲሆን በባንኩ ባለአክሲዮኖችና በክቡራን ደንበኞቹ ብርቱ አጋርነት ካስቀመጠው ስትራቴጂክ ዕቅድና ርዕይ ጋር አብሮ በሚሔድ በሳል አመራርና ትጉሃን ሰራተኞቹ በመታገዝ ከአንድ ቢሊየን 25 ሚሊየን ብር በላይ ትርፍ  ማስመዝገቡን ገልጿል፡፡

ባንኩ በመላው የሀገራቱ ክፍል ተደራሽነቱን በማስፋት ከ225 በላይ ቅርንጫፎች መክፈት የቻለ ሲሆን ቅርንጫፎቹን ዘመኑን በዋጀ የኮር ባንኪንግ ቴክኖሎጂ በማስተሳሰር ለክቡራን ደንበኞቹ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል በማለት በማኅበራዊ ገፆቹ ገልፀዋል። በተጨማሪም በዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎት ዘርፉ 24/7 ደንበኞቹን በማገልገል ላይ ነው፡፡

በዘርፈ ብዙ መለኪያዎች በከፍተኛ የዕድገትና የስኬት ጉዞ ላይ የሚገኘው ባንኩ ወደፊትም ከባለአክሲዮኖችና ከክቡራን ደንበኞቹ ጋር አብሮ በመስራት ይህንኑ ከፍተኛ ውጤት የሚያስቀጥል ይሆናል ብለዋል የባንኩ አመራሮች፡፡

#GlobalBankEthiopia #BankInEthiopia #GBE #Profit
👍2😍1
July 23, 2024 808 3