Forwarded frommars@abc
ሰበር ዜና! የ2015 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ይፋ ሆነ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በዛሬው እለት የ2015 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ማለፊያ ውጤትን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡ ሲሆን በመግለጫቸውም በዘንድሮው ማለፊያ ውጤት 50% እና ከዛ በላይ ያስመዘገቡ መደበኛ ተማሪዎች ወደ ዘጠነኛ ክፍል እንደሚዘዋወሩ ጠቁመው የተለያየ የአካል ጉዳት ላለባቸው ተማሪዎች የማለፊያ ነጥቡ 45% መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዘንድሮ 73,385 ተማሪዎች ፈተናውን ወስደው 70.6% ያህሉ 50 ፐርሰንትና ከዛ በላይ በማምጣት ማለፋቸውን ዶክተር ዘላለም ገልጸው 61,840 ከሚሆኑ የቀን ተማሪዎች መካከል 50,812 የሚሆኑት ማለትም 82.16 % ያህሉ የማለፊያ ውጤቱን በማስመዝገብ ወደቀጣዩ የትምህርት እርከን መዘዋወራቸውን አስረድተዋል፡፡ #mars@abc
July 28, 2023 3.8K 3