ያለፈውን በትምህርትነቱ ፣ ነገን በብልጫነቱ ፣ ዛሬን ግን በተጨባጭነቱ ውደደው ፡፡ ከትላንት ከመማር በቀር ወደ ኋላ መልሰህ ማደስ አትችልም ፡፡ ትላንት ላይ መዘግየት አመድ ላይ እንደ መንከባለል ነው ፡፡ መቆሸሽ እንጂ መንጻት የለውም ፡፡ ታሪክን ትማረዋለህ እንጂ አትቀየመውም ፡፡ ዛሬ ከትላንት የተሻለ እንደሆነ ነገም ከዛሬ የተሻለ ይሆናል ፡፡ ከትላንት ዛሬ እውቀትህ ጨምሯልና ዛሬ ከትላንት ትሻላለች ፡፡ ነገም ከዛሬ የተሻለ ታውቃለህና ብልጫ አላት ፡፡ ነገ እንደፈራኸው አይደለም ፣ ትላንት ላይ ዛሬ ነገ ነበረች ፡፡ እንደ ፈራሃት ግን አይደለችም ፡፡ ቀኑ ላይ ኃይል አለ ፡፡ እግዚአብሔር በቦታው አቅም ይሰጥሃል ፡፡ ራስህን እንደ ገመትከው አይደለህም ፡፡ በአስቸጋሪ ቦታዎች ላይ አቅም ይሰጥሃል ፡፡ በክፉ ቀኖች ቆራጥ ያደርግሃል ፡፡
የከሰርከውን ነገር በገንዘብ እንደ ተማርከው ትምህርት ቁጠረው ፡፡ ያገኘኸውን እንደምታጣው አድርገህ ያዘው ፡፡ የምትመኘውን በትዕግሥት ጠብቀው ፡፡ ወደፊት ምን ይመጣ ይሆን ብለህ አትጨነቅ ፡፡ የፈራኸው ቢመጣም ከዚህ በላይ አትታወክም ፡፡ ባልመጣ ቀን የመጣውን ቀን አትረብሸው ፣ የመጣውን ቀን ትተህም ባልመጣ ቀን አከናውናለሁ አትበል ፡፡ አንተ የአሁን ሰው ነህ ፡፡ ስትተኛ ለመንቃትህ ፣ ስትወጣ ለመመለስህ ምንም ዋስትና የለህም ፡፡ በማይረቡ ነገሮች አእምሮህን አታጣብ ፡፡ ችግሮችን ከምንጫቸው ትተህ ከወራጁ ከገደብህ ይደገማሉ ፡፡ እነዚያን ክፉ ቀኖች ካልረሳህ ዛሬን ይረብሻሉ ፡፡ ፍቅር የሰጡህን ሰዎች ካላመሰገንህ ነፍስህ በውለታ እስረኛ ትሆናለች ፡፡ ሞተህም የምትወቀሰው አደራ በማጥፋትህ ነውና ታማኝ ሁን ፡፡ የሞተ ሰው የገደለውን ያውቃል ፣ ነገር ግን ነቅቶ አይከስስም ፡፡ ትልቁ ዳኛ ጋር እየሄደ ነውና ፡፡ እግዚአብሔር ከተናገረልህ አንተ ዝም በል ፡፡ እግዚአብሔር ሲናገር አንተ ከተናገርህ ሁሉን ነገር ታበላሻለህ ፡፡
- .....እንዴት #አደራችሁ ?
- .....እንዴት #አረፈዳችሁ ?
- .....እንዴት #ዋላችሁ ?
- .....እንዴት #አመሻችሁ ?
JOIN @Applied_CHRISTIANITY



