አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ነሐሴ አሥራ ስድስት በዚች ቀን አምላክን የወለደች የእመቤታችን ድንግል ማርያም ሥጋዋ ወደ ሰማይ ያረገበት መታሰቢያዋ ሆነ።
ከዕረፍትዋም በኋላ ከእነርሱ ስለመለየትዋ ሐዋርያት ፈጽመው ያዝኑ ነበር.. ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ተገለጠላቸው እርሷን በሥጋ ያዩዋት ዘንድ እንዳላቸውም ተስፋ ሰጣቸው።
.
.
በወርሃ ነሐሴ በ16ኛው ቀንም፥ ዳዊት “በቀኝህ ንግሥቲቱ ትቆማለች” ብሎ ትንቢት እንደተናገረው በልጇና በጌታዋ ቀኝ ተቀምጣ፣ በመላእክት ሠራዊት ተከባ አዩዋት።
ጸሎቷ ልመነዋ ከሁላችን ክርስቲያኖች ጋር ይሁን አሜን
[ሥንክሳር ዘወርሃ ነሐሴ]
@Apostolic_Answers



