ጄኔራሉ ከህውሃት አምልጠው አዲስ አበባ ገቡ‼
በትግራይ ክልል ያለውን ውጥረት እና የርስ በርስ ፍጥጫ ተከትሎ፣ ሜጀር ጄኔራል ተክለብርሃን ወልደአረጋይ (ጄኔራል ሳንቲም) "ወደ አዲስ ጦርነት መግባት አልፈልግም" በሚል ጠንካራ አቋም ከህውሃት አምልጠው ከመቀሌ ወደ አዲስ አበባ መመለሳቸው ታውቋል።
ይህ የጄኔራሉ ውሳኔ ችግሮችን በሚሊታንትነት ሳይሆን በምክንያታዊነት እና በተቋማዊ አሰራር ለመፍታት ካላቸው ጽኑ እምነት የመነጨ መሆኑን ተንታኞች ገልጸዋል። እርምጃቸውም በክልሉ ውስጥ ለሚታየው የጦርነት ቅስቀሳ ግልጽ የተቃውሞ መልዕክት አድርገው ታዛቢዎች ወስደውታል።





















