በሳን ፍራንሲስኮ የሚገኘው Andon Market የተሰኘ ሱቅን በስራ አስኪያጅነት ሲመራ የነበረው 🤶 Claude የተሰኘው የ-AI ሞዴል የመጀመሪያውን የሰው ሰራተኛ ከስራ አሰናበተ ➡️በሳን ፍራንሲስኮ ውስጥ ትክክለኛ ሰራተኞች እና የቅጥር ውል ባሉበት Andon Market ውስጥ Claude የስራ አስኪያጅነት ሚና የተሰጠው ሲሆን፣ በ23 የስራ ቀናት ውስጥ 17 ጊዜ ያረፈደን አንድ ሰራተኛ ከስራ አሰናብቷል። ይሁን እንጂ ውሳኔው ሙሉ በሙሉ በ-AIው በራስ ገዝነት የተወሰነ ሳይሆን፣ መጀመሪያ ላይ ችግሩን ችላ ብሎ ካለፈ እና የማስጠንቀቂያ ሀሳብ ከሰጠ በኋላ ከ-Andon Labs ሰራተኛ በቀረበለት አቅጣጫ ጠቋሚ ጥያቄ (Leading question) አማካኝነት የተወሰነ ነበር። ➡️የንግድ እንቅስቃሴውም ፈታኝ ሁኔታ የገጠመው ሲሆን ባለፉት 5 ወራት ውስጥ የሱቁ ካፒታል ከ$100,000 ወደ $61,000 ዝቅ ብሏል ከሰራተኞቹ አንዱም በ-AI ቁጥጥር ስር መስራትን “የሚያስጠላ እና የሚያቅለሸልሽ” (Nauseating) ሲል ገልጾታል። ይህ ሙከራ የ-AI ሞዴሎች የሰው ኃይልን እና የንግድ ስራዎችን በቀጥታ የመምራት አቅማቸው ገና በርካታ ውስብስብ ፈተናዎች እንዳሉበት ያሳያል። 🤩 @AddisIntel
August 18, 2026 81