ዛሬ 33ኛውን ከተማ አቀፍ የትምህርት ጉባኤ “ብሩህ ነገን በዛሬ አዕምሮዎች” በሚል መሪ ቃል አስጀምረናል።… — Addis Ababa Design And Construction Works Bureau — TG.ME

ዛሬ 33ኛውን ከተማ አቀፍ የትምህርት ጉባኤ “ብሩህ ነገን በዛሬ አዕምሮዎች” በሚል መሪ ቃል አስጀምረናል።

ይህ ጉባኤ በየዓመቱ የምናካሂደው የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ፣ ተደራሽነትን ለማስፋት፣ የመማር ማስተማር ሂደቱን ጤናማ እና ውጤታማ ለማድረግ፣ በዘርፉ የተሰሩትን ጠንካራ ስራዎች ልምድ የምንቀምርበት፣ የሚታረሙትንም ለይቶ በጋራ መፍትሄ የምንሰጥበትና በጋራ እቅጣጫ የምንይዝበት ጉባኤ ነው ።

የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በከተማ አስተዳደራችን በልዩ ትኩረት ሰርተን የተማሪዎች ውጤት እየተሻሻለ መጥቷል። ዛሬ በከተማችን የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ውጤት ወደ 33 በመቶ መሻሻል አሳይቷል። ነገር ግን አሁንም ከፍ ያለ ውጤት እንጠብቃለን፤ ገና ብዙ መሥራት ይጠበቅብናል።

መምህራን፤ ባለድረሻ አካላት በእልህ ሰርተን መፍጠር የሚችሉ፣ ችግር የሚፈቱ፣ በሥነ ምግባር የታነፁ፣ እውቀት የታጠቁ ተማሪዎችን በብዛት ለመፍጠር መረባረብ ይጠበቅብናል።

ከተማ አስተዳደራችን ዋናውን ኢንቨስትመንት ትምህርት ላይ እናውል ብለን፣ ትልቁን በጀት ለትምህርት ዘርፍ እንዲሆን አድርገናል። ትውልድ ላይ ከመሰረቱ መስራት ወሳኝ በመሆኑ፣ ዋና የእዕምሮ እድገት በጨቅላ ህፃንነት ወቅት በመሆኑ ቀዳማይ ልጅነት ላይ እየሰራን እንገኛለን። በዚህ አግባብ ከመሰረቱ ጀምረን እየሰራን በአንደኛ ደረጃ እንዲሁም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ ከፍተኛ ውጤት እና በዲሲፕሊን የታነፀ ትውልድ እንጠብቃለን።

እስካሁን በተገኘው ውጤት ሁላችሁንም ከልብ እያመሰገንኩ፤ በቀጣይም በእውቀት የበለፀጉ፣ በስነምግባር የታነፁ፣ አልቀው የሚሰሩ ተማሪዎች ለመፍጠር ከልብ፣ ዋጋ ከፍለን ተባብረን እንድንሰራ አደራ እላለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ
👍2❤1
September 1, 2026 957