ኢብራሂም ቱፋ ጠ/ሚን ነቢይ እንዳልልህ ከነቢዩ ሙሀመድ በኋላ ነቢይ የለም ተብሏልና ወሊይ ብዬሃለሁ አለ (አዑዙ ቢላህ)
———
የኢኽን አል-ሙስሊሚን ነገር ካላቸው የስልጣን ጥማትና ስካር የተነሳ መቼም ምን ተናገሩ? ተብሎ የሚደንቅ ነገር ባይኖረውም፣ የሚደንቀው ግን "የመጅሊስ ሰዎች ሽበት ያበቀሉ በሳሎች ናቸው…" የሚሉ ሰዎች ናቸውና ለነዚህና መሰል ሰዎች ሸይኽ ጧሀ ኸድር (ሀፊዘሁላህ) እንዲህ በማለት ይጠይቋቸዋል:- “እናንተ የቀደምቶችና አዲሶቹ የተምይዕ ጌቶች ሆይ! በእርጥም አላህ በመንገድ አጋሮቻችሁ ምክንያት ፈትኗችኋል፣ እርሱም ያ የመጅሊሳችሁ መሪ የሆነው ሰው ከባድ የሆነን ውግዝ ንግግር በውሸት ቃል አጊጦ ይዞላችሁ ተከስቷል፣ የነቢይነትን ደረጃ ለጠ/ሚሩ የተገባች አድርጓል፣ ነቢይነት የተደመደመ ባይሆን ኖሮ የነቢይነትን ማእረግ ሰጥቶት ነበር። በዚህም አልተብቃቃም ወሊይነትን የተገባ አድርጎለታል።
=> እናንተ የባሌ ሰዎች ሆይ! ሁለት ጊዜ ወደነቢይነት ደረጃ ለመሞገት የሚጣጣርን ሰው በተክቢርና በጭብጨባ ለማጀብ ነፍሳችሁ እንዴት ወደደች? እንዲሁም ከአመት በፊት በዙህድ ዙሪያ በመጡ ነቢያዊ ሀዲሶች ላይ አህመዲን ሲያላግጥ በሳቅ አጅባችሁ አሳለፋችሁት፣ አሁን ደግሞ እለተ ቅዳሜ 17/3/1448 ዓ.ሂ ላይ የመጅሊሳችሁ መሪ ሀጂ ኢብራሂም የነቢይነትን ማእረግ ለመስጠት ሲዳዳው ከዚያም በኋላ ወሊይ ሲያደርግ በተክቢር፣ በተህሊልና በጭብጨባ አጀባችሁት!!
በውስጣችሁ ቅን የሆነ ሰው የለምን?!
ነፍሳችሁ እንዴት ይህን ወዳ ተቀበለች?!
✍🏻ትርጉም:- ኢብን ሽፋ
#Join ↘️↘️ ቴሌግራም ቻናል
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa
Forwarded fromطه خضر أبوعبد الله
Telegram
ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa
እራስህን ሁል ጊዜ ለቁርኣንና ለሀዲስ ተጎታች አድርግ!
በአንድ ነገር ላይ ከቁርኣንና ከሀዲስ ማስረጃ ሳታገኝ አቋም አትያዝ!
ሁሌም ለሰዎች መልካምን ተመኝ!
ለሀቅ እንጂ ለሰዎች ወጋኝ አትሁን

August 31, 2026 416 6