AARB Arada Branch Customer service: post #182 — TG.ME

ሠላም ውድ ግበር ከፋዮቻችን የE-Clearance (Online ክሊራንስ) አገልግሎት መጀመራችንን እያሳወቅን። በዚሁ መሰረት የE-Clearance (Online ክሊራንስ) አገልግሎቱን ተጠቃሚ መሆን የሚችሉ ግብር ከፋዮች እና ማሟላት የሚጠበቅባችሁ ምን ምን እንደሆነ ለማሳወቅ እንወዳለን *የE-Tax አገልግሎት ተጠቃሚ የሆኑ ኢፋይል የሚያደርጉ ግብር ከፋዮች *ኦዲት የማያስፈልጋቸው የክሊራንስ አይነቶችን የሚጠይቁ ግብር ከፋዮች *ቅሬታ ላይ ወይም ፍርድ ቤት ላይ ከሆነ አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶችን ማያያዝ የሚችሉ ግብር ከፋዮች *የሚጠበቅባቸውን ሁሉንም የግበር ዓይነት ግብር ያሳወቁና የከፈሉ *ከላይ የተያያዘ ቃለ መሀላ ፎርም ተሞልቶ ማያያዝ ለምሳሌ ፡- Schedule-C, VAT, Excise Tax, Schedule-A, Pension ማስታወሻ ፡ ከታክስ ሴንተሩ ወይም ከቅርንጫፋችን ተጨማሪ መረጃ እንድታማሉ ቴክስት ሊላክላችሁ ስለሚችል View Message ላይ እየገባችሁ የተጠየቃችሁትን መረጃ እንድታሟሉ ካልሆነ ክሊራንሱ አይሰራላችሁም በተጨማሪም የE-Clearance አጠያየቅን የሚያሳይ በዚሁ ቴሌግራም አጭር ቪዲዮ የለቀቅን መሆኑን እናሳውቃለን

March 31, 2026 2.9K 2 4