"በትግራይ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ከወታደራዊ እንቅስቃሴ ነፃ ካልሆኑ ተማሪ አንመድብም" - ትምህርት ሚኒስቴር
በትግራይ ክልል በሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ግቢ ውስጥ የሚገኙ ታጣቂዎችና የወታደራዊ ኃይሎች እንቅስቃሴ በአስቸኳይ እንዲነሱ ትምህርት ሚኒስቴር ጥብቅ ማሳሰቢያ አስተላለፈ።
🔹 ዋና ዋና ነጥቦች፦
የተተላለፈው ማሳሰቢያ፦ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ለመቀሌ፣ አክሱም፣ አዲግራት እና ራያ ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዚዳንቶች በላኩት ደብዳቤ፣ የዩኒቨርሲቲዎቹ ግቢዎች ከማንኛውም ወታደራዊ እንቅስቃሴ ነፃ እንዲደረጉ አሳስበዋል።
የተማሪዎች ደህንነት፦ በካምፓሶቹ ውስጥ የወታደራዊ ኃይሎችና የትጥቅ እንቅስቃሴዎች መኖራቸው የተማሪዎችን ደህንነትና ሰላማዊ የመማር-ማስተማር ሂደት አደጋ ላይ እንደሚጥል ሚኒስቴሩ ገልጻል።
የሚኒስቴሩ ማስጠንቀቂያ፦ የዩኒቨርሲቲዎቹ ግቢዎች ሙሉ በሙሉ ከወታደራዊ እንቅስቃሴ ነፃ መሆናቸው ካልተረጋገጠ ሚኒስቴሩ ወደ ተቋማቱ ተማሪዎችን እንደማይመድብ አስታውቋል።
@AAU_GENERAL

3September 7, 2026 703 4