ጳጉሜ 3 የፅናት ቀንን በማስመልከት የዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል ለ153 ዜጎች ነፃ ምርመራና ሕክምና… — Addis Ababa Health Bureau / አዲስ አበባ ጤና ቢሮ / AACAHB / — TG.ME

ጳጉሜ 3 የፅናት ቀንን በማስመልከት የዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል ለ153 ዜጎች ነፃ ምርመራና ሕክምና አገልግሎት ሰጠ።

አ አ ጤና ቢሮ ጳጉሜ 3/2018 ዓ.ም.

በአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ጤናቢሮ ስር ከሚገኙ ሆስፒታሎች አንዱ የሆነው የዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል ጳጉሜ 3 የጽናት ቀንን በማስመልከት በ2018 ዓ.ም. የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሃ ግብር አካል የሆነው ነፃ የምርመራና ሕክምና አገልግሎት ለ153 ዜጎች ታካሚዎች ሰጥቷል።

ሆስፒታሉ በመሿለኪያ አካባቢ በሚገኘው የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ሠራተኞች ነፃ የጤና አገልግሎት ነው የተሰጠው።

በህክምና አገልግሎቱ 105 ሰዎች የደም ግፊትና የደም ስኳር ምርመራ ያገኙ ሲሆን፣ 28 ሰዎች ደግሞ ነፃ የጥርስ ሕክምና አገልግሎት ተጠቃሚ ሆነዋል።

በተጨማሪም የማኅፀን በር ካንሰር የምርመራ መሣሪያዎችን ወደ አገልግሎት ቦታው በማጓጓዝ ለ20 የተቋሙ ሴት ሰራተኞች የማህፀን በር ካንሰር ምርመራና አስፈላጊው ሕክምና ተሰጥቷል።

የጽናት ቀንን በማስመልከት የተካሄደው የህክምና አገልግሎት ቢሮው በቀጣይም ለማኅበረሰቡ ተመሳሳይ መርሃ ግብሮችን አጠናክሮ ተደራሽ ማድረጉን ይቀጥላል ።

ለህብረተሰቡ ጤና ሁልጊዜ በትጋት እንሰራለን !
September 8, 2026 1.3K