Update‼
የ4 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 24 ሰዎች ቆስለዋል‼
በአፋር ክልል አሚባራ ወረዳ «ብርጌድ» ድልድይ አካባቢ ዛሬ ህዳር 13 ቀን 2019 ዓ.ም. በሕዝብ ማመላለሻ ታታባስ ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ4 ሰዎች ህይወት ማለፉንና በ24 ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የወረዳው ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ። ፖሊስ ተጎጂዎችን ወደ ሆስፒታል የማድረስና መንገዱን የመክፈት ሥራ እያከናወነ ይገኛል።
November 23, 2026 172