እሷ አትከንፍም ከመጣው ጊዜ ከነፋሱ
ወግ ይዛለች መርጣ ፈትሻ ቀድማ ብዙ
አያረጅም ዘመን አልፎበት ቅን ውበቷ
በእውነት ክብር የተረጋጋው ሴትነቷ
ልቅደም ማትል ወታ አቅፋ ምትውል ከቤት
እማኝ አላት ብዙ ለሷ ለኔ እመቤት
በእንቁ ከደመቀው ከአንባር ባለድሪ
ባትሮጥም እሷ ነች በሀገሩ ተጠሪ
ፈጥነው እያለፏት አርገዋት ቀርፋፋ
ቆመው ደግሞ ያይዋታታል ሲደክማቸው አልፋ
አጉል ተቸኳኩላ ተጣድፋ ባትሮጥም
ሰክናም እየሄደች ጊዜ አይረፍድባትም
ጨዋነቷ ነው ሴትነቷ
ዘበናይቷ
Dan admassu


