እግዚአብሔርን ጉልበቱ ያደረገ ሰው በመሄድ አይደክምም
💥 የመጣነውን መንገድ ሁሉ የመጣንበት ስውር ጉልበታችን እግዚአብሔር ይባላል።
✍️ በመኖር ውስጥ ያሉ በውጣ ውረድ የተሞሉ የህይወት ጎዳናዎች የሰውን ልጅ ከፀሐይ በታች የሚፈትኑ ድምፅ አልባ ተግዳሮቶች ናቸው። መኖርን በጣም ቀላል የሚያድርግላችሁ ምስጥር ቢኖር እግዚአብሔርን ጉልበት ማድረግ ይባላል።
👉 እግዚአብሔርን ጉልበቱ ያደረገ ሰው ሰውም ካለው ሰው የዚህን ዓለም ነዋይም ከሰበሰበ ሰው ይልቅ የመኖሩ አቅሙ የላቀ ነው። እግዚአብሔር በሚሰጣችሁ ዓመታቶች ያለ መታከትና ያለ መዛል ለመኖር እግዚአብሔር በቂና ከበቂ በላይ ነው።
🤚በህይወት ለመቀጠል ጉልበት ለሌላችሁ ሰዎች ከዚህ ቀን ጀምሮ እግዚአብሔር ጉልበት ይሁንላችሁ!!!
26July 8, 2026 3.2K 1 18