በአሜሪካ ሚቺጋን ግዛት የሪፐብሊካን ፓርቲ የፕራይመሪ ምርጫ ላይ የተከሰተው ታሪክ፣ ማንነቱን ለሚክድና ሃይማኖቱን ለዱንያ ጥቅም ለሚሸጥ ሁሉ ትልቅ ማስተማሪያ ነው።
አሚር ሀሰን የተባለው ግለሰብ፣ ቀድሞ ሙስሊም የነበረና በኋላ ግን ሃይማኖቱን ቀይሮ ክርስቲያን መሆኑን ያወጀ ሰው ነው። ይህ ሰው በጽንፈኛ ፖለቲከኞች ዘንድ ተቀባይነትን ለማግኘት ሲል፣ እጅግ አክራሪ፣ ፀረ-ሙስሊምና ፀረ-ስደተኛ አቋሞችን ማንጸባረቅ ጀመረ።
በዚህ የክህደት መንገዱም ከቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ ከኮንግረስ አፈ-ጉባኤ ማይክ ጆንሰን እና ከሴናተር ቲም ስኮት ሳይቀር ሙሉ ድጋፍን (Endorsement) አገኘ። በገንዘብም በኩል ከፍተኛ ዶላር በማሰባሰብ፣ "አሁንማ ማንም አያቆመኝም" ብሎ የተመካበት ጊዜ ነበር።
ነገር ግን የአላህ (ሱ.ወ) ጥበብና ፍትህ አስገራሚ ነው። የቱንም ያህል ማንነትህን ብትክድና ሙስሊሞችን ብትጠላም፣ ፀረ-ሙስሊም የሆኑ ዘረኞች መቼም ቢሆን በሙሉ ልብ አይቀበሉህም። አሚር ክርስቲያን ነኝ ብሎ ቢምልም፣ ዘረኞቹ መራጮች ስሙ "አረብኛ/ሙስሊም" ስለሚመስል ብቻ አላመኑትም፤ ድምፃቸውንም ነፈጉት። ከዚህም በላይ አላህ ይህንን ግለሰብ ያዋረደውና መሳለቂያ ያደረገው በጠንካራ ተፎካካሪ እጅ አይደለም!
አሚር የተሸነፈው ቶም ስሚዝ ለተባለ ግለሰብ ሲሆን፣ ይህ አሸናፊ ሰው፦
⛳️ በፌስቡክ ገጹ 95 ብቻ ተከታዮች ፎሎወሮች ያሉት፣
⛳️ ለምርጫው ከ2,000 ዶላር በታች ያወጣ፣
⛳️ እና ከሁሉ በላይ ደግሞ "ከምርጫው ራሴን አግልያለሁ" ብሎ ላሳወቀና "ለሌላ እጩ ድምፃችሁን ስጡ" በማለት ቅስቀሳውን ላቆመ ሰው ነበር!
ከምርጫው ራሱን ባገለለና ምንም ዓይነት የፖለቲካ ክብደት በሌለው ሰው መሸነፍ፣ ተራ ሽንፈት ሳይሆን ታሪክ የማይረሳው መለኮታዊ ውርደት ነው። እምነትን ሸጦ ክብርን ከሰው ልጆች መፈለግ መጨረሻው ኪሳራ ነው። ታላቁ ጌታችን አላህ በቅዱስ ቁርኣን ላይ፣ እውነተኛ ክብር ከማን ዘንድ እንደሚገኝ እንዲህ በማለት ያስጠነቅቃል፡-
“እነዚያ ከምእምናን ሌላ ከሓዲዎችን ወዳጆች አድርገው የሚይዙ እነሱ ዘንድ ልቅናን ይፈልጋሉን ልቅናውም ሁሉ ለአላህ ብቻ ነው፡፡”
— አን-ኒሳዕ (4:139)
የሰዎችን ውዴታ ለማግኘት ሲባል የአላህን መንገድ መተው የሚያስከትለውን አሳፋሪ ውድቀት፣ ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) በሚከተለው ሐዲሳቸው እንደሚከተለው ገልጸውታል፡-
"አላህን በማስቆጣት የሰዎችን ውዴታ የፈለገ ሰው፣ አላህም በእርሱ ላይ ይቆጣል፤ ሰዎችንም በእርሱ ላይ ያስቆጣበታል።" (ሱነን አል-ቲርሚዚ 2414)
ሃይማኖቱን ሸጦ ዱንያን ለማግኘት የሞከረ፣ አላህ በዱንያም እንዲህ መሳለቂያ ያደርገዋል፤ የአኼራውም ዕጣ ፈንታ የከፋ ይሆናል። አላህ መጨረሻችንን ያሳምርልን፤ ማንነታችንንና እምነታችንን ጠብቀን፣ ለፈጣሪያችን ብቻ አድረን በክብር የምንኖር ያድርገን!
ፌስቡክ | ዋትስአፕ
116
44
1August 9, 2026 6.7K 1 10