ክርስትናን በርግጥ የመሰረተው ማነው?
ዛሬ በስፋት የሚታወቀው የክርስትና ሃይማኖት ክርስቲያኖች እንደሚያምኑት በቀጥታ በኢየሱስ ክርስቶስ የተመሰረተ ሳይሆን፣ በጠርሴሱ ጳውሎስ የተቀረጸ መሆኑን የሚከራከሩ የታሪክና የነገረ-መለኮት ምሁራን አሉ። ጳውሎስ በሥጋ አይቶትም ሆነ አግኝቶት የማያውቀውን የኢየሱስን ታሪካዊ ህይወት ወስዶ፣ ኢየሱስም ሆነ የመጀመሪያዎቹ ደቀመዛሙርት ወደማያውቁት አዲስ የድነት ርዕዮተ-ዓለም ቀይሮታል። ከእርሱ በፊት ከነበሩት የኢየሱስ የቅርብ ተከታዮች ትምህርት የተለየ እና የሙሴን ህግጋት የሚሽር አዲስ ወንጌል ይዞ ብቅ ማለቱ፣ ከመጀመሪያዋ የኢየሩሳሌም አማኝ አባላት እና ከኢየሱስ ተከታዮች ጋር ከፍተኛ የሥነ-መለኮትና የስልጣን ሽኩቻ ውስጥ ከትቶት ነበር።
ይህንን ሃሳብ ታዋቂው የታሪክ ምሁር ሃያም ማኮቢ በመጽሐፋቸው በሰፊው ዳስሰውታል። ማኮቢ እንዳብራሩት፣ የጳውሎስ ትምህርት ከንጹሑ የኢየሱስ አስተምህሮ የተገኘ ሳይሆን፣ በዘመኑ ከነበሩት የግሪክ ጣዖት አምልኮዎች የተቀዳና የኢየሱስን ትክክለኛ መሲህነት ያዛባ አዲስ ሃይማኖት ነው። በመሆኑም ዛሬ የምናየው ክርስትና የኢየሱስን ቀጥተኛ አስተምህሮ ሳይሆን፣ ጳውሎስ የራሱን ራእዮች እና አመለካከቶች ተጠቅሞ የፈጠረውን እምነት መሆኑን መገንዘብ እንችላለን።
• Hyam Maccoby, The Mythmaker: Paul and The Invention of Christianity, Chapter 1: The Problem of Paul.
.
.
⛳️ በዚህ ጉዳይ እንቀጥላለን!
ፌስቡክ | ዋትስአፕ

80
18
12August 8, 2026 5.9K 2 13