ዐረገች በስብሐት ዐረገች በስብሐት ዐረገች በእልልታ በስብሐት በእልልታ አረገች አረገች በእልልታ የጻድቃን… — የያሬድ ውብ ዜማ⛪⛪🕇🕆 — TG.ME

ዐረገች በስብሐት ዐረገች በስብሐት ዐረገች በእልልታ በስብሐት በእልልታ አረገች አረገች በእልልታ የጻድቃን እመቤት የኃጥአን ተስፋ ዐረገች ዐረገች በእልልታ አዝ የማይታበለው እንዲፈጸም ቃሉ ብታርፍም እመ አምላክ ቤዛዊተ ኩሉ ዐረገች ተነስታ ድንግል የኛ እናት እልል በሉላት እልል በሉላት አዝ ሰማያት ተደንቀው በአዲሲቷ ሰማይ ያልቻሉትን ጌታ ወስናው ብትታይ ሊቀበሏት ወጡ በሀሴት በሙሉ ነዪ ነዪ እያሉ ነዪ ነዪ እያሉ አዝ ዘመኗን በሙሉ ስለ ልጇ አልቅሳ የመከራ ሰይፍን አሳልፋ ነፍሷ በቀኙ ልትቆም ንግሥት እየተባለች ይኸው ዐርጋለች ይኸው ዐርጋለች አዝ በሐዋርያት አበው ትምሕርት የጸናችሁ የልጇ ምሥክር ከዘሯ የቀራችሁ ከሞት ተነሥታለች ቅድስት እናታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አላችሁ አዝ እጅሽ በዳሰሰው በነካው ሰበን እንደ ባረክሻቸው ሐዋርያቱን ማርያም ማርያም ስንል ደጅሽ ላይ ቆመን እኛንም ባርኪን እኛንም ባርኪን             መዝሙር ዘማሪ ዲያቆን አማን ኡርጌሳ

August 11, 2026 1.7K 34