ድንግል ወላዲተ ቃል ድንግል ወላዲተ ቃል(፪) አሟሟዋትሽ በጥር ነሐሴ መቃብር - - ድንግል ያንቺ ለብቻ ነው ትንሳኤሽ ሲነገር - - ድንግል ስጋሽ በምድር ላይ የታለ እንደፍጡር - - ድንግል አርጓል ወደ ሰማይ ከክርስቶስ መንበር - - ድንግል ድንግል ወላዲተ ቃል(፪) ስጋሽን ሲያሳርጉ መላክት ከሰማይ - - ድንግል ቶማስ በደመና ሲመጣ መንገድ ላይ - - ድንግል መግነዝ ተረከበ ለሐዋርያት ሊያሳይ - - ድንግል ድንግል ወላዲተ ቃል(፪) ትንሳኤሽን ሽተው ግራ ሲገባቸው - - ድንግል ሐዋርያት ጾመው ተገልጥሽላቸው - - ድንግል ተቀብራ አልቀረችም በምድር ከደጅዋ - - ድንግል ወደላይ አረገች እርሷም እንደልጅዋ - - ድንግል ድንግል ወላዲተ ቃል(፪) ለማየት ሲጓጉ የድንግልን ትንሳኤ - - ድንግል እርገቷን አወቁ በልዩ ሱባኤ - - ድንግል እኛም እንጸልይ በራችንን እንዝጋ - - ድንግል ከወላዲተ አምላክ እንድናገኝ ዋጋ - - ድንግል
August 11, 2026 1.4K 19