# ድንግል_ትንሳኤሽን# ድንግል ትንሳኤሽን እስከምናይ ድረስ ገብተናል ሱባኤ ባንድነት በመንፈስ ለእኛ እስከሚገለጥ ቶማስ ያየው እውነት አንወጣም ከደጅሽ ኪዳነ ምህረት /፪/ ሞትን የረገጠ ልጅሽ ካንቺ ጋር ነው ውጦ የሚያስቀርሽ የቱ መቃብር ነው የዕርገትሽን ዜና ከቶማስ ስምተናል ትንሳኤሽ እውነት ነው ስበንሽን አይተናል ሞትማ በሞት ተሽንፏል ባንቺ ላይ እንዴት ኃይል ያገኛል /፪/ ልናየው ወደድን የቶማስን ክብር ለምን ተስወረን የትንሳኤሽ ሚስጢር በራችንን ዘግተን በፀሎት ወድቀናል ተገልጠሽ አብሪልን ልጆችሽ ናፍቀናል ሞትማ በሞት ተሽንፏል ባንቺ ላይ እንዴት ኃይል ያገኛል /፪/ መዝሙረኛ አባትሽ ዳዊት ጽፎልናል ሞትን የማያይ ስው ማን አለ ብሎናል ይህ እውነት በዘመን አንቺ ላይ ቢደርስም በሞት ተሽንፏል መቃብር አይኖርም ሞትማ በሞት ተሽንፏል ባንቺ ላይ እንዴት ኃይል ያገኛል /፪/ ቶማስ ከደመናው ወርዶ ሲያናግረን ስለ ሆነው ነገር እጅጉን ተመስጥን እኛም ይህን ክብር ተመኘን ለማየት ድንግል አሳስቢልን ኪዳነ ምህረት ሞትማ በሞት ተሽንፏል ባንቺ ላይ እንዴት ኃይል ያገኛል /፪/
August 11, 2026 1.5K 14