ደብረ ታቦር ተሞላ በግርማው ብርሃን ከበበው አሸብርቋል ረጅሙ ተራራ ክብሩ ሲያበራ ክብሩ ሲያበራ..... ጴጥሮስና ያዕቆብ ደግሞ ዮሐንስን ዩዟቸው ተጓዘ የወረጣቸውን በፊታቸው ሳለ ድንገት ተለወጠ ኢየሱስ ሲያበረ ልባቸው ቀለጠ ክብሩ ሲያበራ.... ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ታዯቸው ጴጥሮስ በተመስጦ ዳስ እንስራ አላቸው ፍቅሩን የቀመሰ አይመኝም ሌላ ክርስቶስ ነውና እውነተኛ ተድላ ክብሩ ሲያበራ.... በእርሱ ደስ የሚለኝ ልጄ ይህ ነውና ስለመዳናችሁ ስሙት በጽሞና ብሎ ሲመሰክር የሰማይ ንጉሱ ከኢየሱስ በቀር አላዩም ሲነሱ
August 2, 2026 3.1K 50