#ታቦር_አበራ ታቦር አበራ ምድርን ከደናት ያደመና እንቅልፍ የለንም ታላቅ ነጎድጕድ ሆኗልና አነቃን ለምስጋና #አዝ ሙሴም የቀደመው ሰዉ ኤልያስ ኃይለኛው ተገኝተዋል በታቦር ምስክርህ ሆነው እኛም ከገናናው ክብር ያባቱን ቃል ሰምተናል በረዶ ሆኗል ልብሱ እፁብ እፁብ ብለናል #አዝ ቃል ገብተህልኝ ነበር ልታሳየኝ ክብርህን ንገስ ከሞት ገስግሰህ አይቸሃለሁ አሁን የሳት ፈረሶች አሉህ ታዋጊው የኔ ጌታ አርሙኒየም ደስ አለው ስሳራን ስለመታ #አዝ እጠብቅሃለሁኝ በምታልፍበት ቆሜ መብራቶቼን አብርቼ ነጩን ልብስ ተሸልሜ የዳዊት ልጆይ ግባ ኢየሱስ ወደቤቴ ብልኤል እልሀለሁ ድናለች ሰውነቴ #አዝ ሁሉንም ብታከብር ሁሉንም ብትምረው ማነው ቸርነትህን የሚከለክለው ጠዋትም የተጠራ አምሽቶ የገባው ሆነዋል ባለዋጋ ከበዛው ስጦታው #አዝ የረዳኸው ይናገራል ያሰበከው በሕይወቱ አቤነዘር እያለ ይዘምር ባንደበቱ በደስታየም ቀን አለህ አይሃለሁ ከጎኔ ከነጋር አልቅሰሃ አሳዝኖህ ሀዘኔ
August 2, 2026 2K 49