#ዛሬ_ተገለጠ የታቦር ተራራ ምንኛ ታደለች/2/ ከተራሮች ሁሉ በብርሃን አጌጠች/2/ ዛሬ ተገለፀ በደብረ ታቦር/2/ የመለኮት ክብር ጴጥሮስም ተመኘ ተከላን ሊሰራ/2/ ልምላሜውን አይቶ በታቦር ተራራ/2/ ዛሬ ተገለፀ በደብረ ታቦር/2/ የመለኮት ክብር ድንገት ብለው ቆዩ ነብያት አርድእት/2/ ተገለጠላቸው ኃያሉ መለኮት/2/ ኃያሉ መለኮት ዛሬ ተገለፀ በደብረ ታቦር/2/ የመለኮት ክብር ሁሉም አላወቁም ከወዴት እንዳሉ/2/ ያን ጊዜ ሲገለፅ የመለኮት ኃይሉ/2/የመለኮት ኃይሉ ዛሬ ተገለፀ በደብረ ታቦር/2/ የመለኮት ክብር የኪሩቤል አምሳል ደብረ ታቦር ናት/2/ ሠማያዊ ንጉስ የከተመባት/2/ የከተመባት ዛሬ ተገለፀ በደብረ ታቦር/2/ የመለኮት ክብር
August 2, 2026 1.7K 46