🎉 Welcome to Victory Academy
ከተማሪዎቻችን የተሰጡ አስተያየቶች👇
https://t.me/victorystcom_7
ስለ Victory academy አጠቃላይ መረጃ
🌟የኢንትራንስ ተፈታኞች እንዲሁም የ 11ኛ ክፍል Natural science ተማሪዎች ቪክትሪን ስትጠቀሙ የምታገኟቸው የትምህርት አይነቶች
📌English , Maths , Physics Chemistry , Biology
📌English , Maths , Economics , Geography , History ናቸው።
🌟የትምህርቶቹ አወቃቀር
ኢንትራስ ከ 600 በላይ ባመጡ ተማሪዎች እና መምህራን የሰፊ ጊዜ ጥናት በማድረግ ከትምህርት ሚኒስቴር ካላቸው ልምድ እና ከሌሎችም መረጃዎችን በመሰብሰብ ትምህርቶቹ ከ9-12ኛ ክፍል በሚከተለው መንገድ ተዋቅረዋል።
1️⃣ኢንትራንስ ተኮር(entrance targeted technique)፦ ይህ ማለት በኢንትራንስ ላይ ብዙ ጥያቄዎች የሚወጣባቸውን እና በዩኒቨርሲቲም ደረጃ እጅግ በጣም አስፈላጊ የሚባሉ ምዕራፎችን በማውጣት ተማሪዎች የተወሰኑ ምዕራፎችን በምንበብ ብቻ ውጤታማ እንዲሆኑ ማስቻል ነው።
✨በዚህ መንገድ(ስልት) በተለይም ኢንትራንስ 3 እና 2 ወር ሲቀራቸው አንብበው የገቡ ልጆች ከማለፍ አልፈው ለማመን የሚከብዱ ውጤቶችን ሲያመጡ ያየንበት እና ልጆችም የመሰከሩለት መንገድ ነው።
2️⃣ተመሳሳይ ይዘት ያላቸውን ምዕራፎች አንድ ላይ በማካተት(Marging and Integration technique) :- ይህ አይነቱ ስልት በተለያየ ክፍል ላይ ያሉ ምዕራፎች ሆነው ነገር ግን ተመሳሳይ (አንድ አይነት) ይዘት ያላቸውን ምዕራፎች አንድ ላይ በማድረግ ከቀላሉ ወደ ከባዱ በመሄድ አያይዞ መስጠት ነው። በዚህ የማቀናጀት ሂደት ውስጥ ተማሪው በትንሹ ሁለት ምዕራፎችን ሳያውቀው እና ሳይሰለቸው ይጨርሳል።
ለምሳሌ፦ የፊዚክስ(Physics) እና ኬሚስትሪ(Chemistry) ትምህርቶች አብዛኛው ምዕራፎች በዚህ አይነቱ ውጤታማ ስልት የተዘጋጁ ናቸው።
3️⃣በአንድ ምዕራፎች ውስጥ ብዙ ምዕራፎችን በማካተት (Inclusion technique):- ይህኛው ስልት በትንሽ ልፋት ፣ ብዙ ምዕራፎችን ውጤታማ በሆነ መንገድ ተፈትኖ የቀረበ ግሩም ስልት ሲሆን በዚኛው ስልት ተማሪዎች አንድ ሰፋ ያለ ምዕራፍ ያነበቡ ቢመስላቸውም በውስጡ ግን ከ 5-7 የሚጠኑ በተለያዩ ክፍሎች በዋናው መፅሃፎቻቸው የተቀመጡ ምዕራፎችን የሚያነቡ ይሆናል።
✨በትንሽ ጊዜ ብዙ እና ሰፊ የነበሩ ምዕራፎችን ያለ ሃሳብ(concept) መጎራረድ በማንበብ ለትልቅ ውጤት ያበቃቸዋል።
4️⃣ከመሰረቱ በመጀመር(Starting from the basics technique)፦ በዚህ ስልት ከባባድ ለሚባሉ ምዕራፎች እንደ ግብዐት የሚያገለግሉ ነገር ግን ቀላል ሆነው ሸዋጅ ጥያቄዎች የሚወጣባቸውን ምዕራፎችን ጥናት በማድረግ ተዘጋጅቷል።
✨በተለይም የኢንትራንስ ጥያቄዎች ቀላል እና ሸዋጅ ከመሆናቸው አንፃር ትኩረት ተሰጥቶበታል።
5️⃣ከባድ ፣ ሰፊ እና ጥልቅ ሃሳብ ያላቸውን ምዕራፎች በማካተት(Difficult, vast and deep chapters technique):- እንደ derivative ,integration , Genetics, Chemical bonding, rotational motion , Electrostatics እና የመሳሰሉትን ምዕራፎች በውስጣቸው ሌሎች ብዙ ምዕራፎችን እንደ ግብዐትነት የያዙ እና ጥልቅ እንዲሁም ብዙ ጥያቄዎች የሚወጣባቸው በመሆኑ በእኛ የትምህርት አሰጣጥ ላይ አካተነዋል።
🌟የትምህርት አሰጣጥ
እንደ ቪክትሪ በዋነኝነት የምናምነው የሚሰጡት ትምህርቶች ሳይሆን ትምህርቶቹ የሚሰጡባቸው መንገዶች የተማሪዎች ውጤት ላይ ትልቅ ለውጥ ያመጣል ብለን እናምናለን።
✨በመሆኑም ከሰፊ ጊዜ ጥናት በኋላ ትምህርቶቹን በብዙ ውጤታማ እና ባልተለመደ መንገዶች አዘጋጅተነዋል።
1️⃣ልቦለዳዊ እና አዝናኝ በሆነ መንገድ ፦ አንድ ተማሪ 300 ገፅ ያለውን ልቦለድ መፀሀፍ በ ቀናት ሲጨርስ በሌላ በኩል 300 ገፅ ያለውን ትምህርታዊ መፅሃፍ ወራት እንዲፈጅበት የሚያደርገው ዋነኛው ልዩነት ልቦለዱ ሲዘጋጅ ምስል ከሳች ፣ ልብ አንጠልጣይ፣ ያልተለመዱ ቋንቋዎችን በመጠቀሙ እና በሳቅ የተሞላ አዝናኝ ጨዋታን በመፍጠር ነው።
✨እኛ ትምህርቶቹን ስናዘጋጅ በዚህ ስልት መሰረት በማዘጋጀት ብዙ ተማሪዎች እኛጋ እየተሳቀቁ ሳይሆን እየሳቁ በቀላሉ ትምህርቶቹን እንዲጨርሱ አስችለናቸዋል። ብዙ ተማሪዎችም በእጅጉ እየተደሰቱ ሲመሰክሩለት ታይቷል።
2️⃣የማገናኘት እና የማዛመድ ጥበቦችን በመጠቀም፦
Chemical bonding-ን ከጋብቻ እና ከጥሎሽ ስረዐት ጋር ፣ Atomic structure-ን ከትልቅ ሰፈር እና ግቢ ጋር ፣ Economics-ን ገበያ ላይ ከምትሸጥ አንድ እናት ጋር\…. ወዘተ በእነዚህ እና በመሳሰሉት መንገዶች ትምህርቶቹን ከነባራዊው አለም ጋር በማዛመድ አገናኝተነዋል።
✨አንድ ተማሪ የChemical Bonding ሃሳቦችን ቢረሳ እንኳን የጋብቻ እና የጥሎሽ ስርዐትን ስለማይረሳ አዛምዶ እንዲይዝ ያስችለዋል።
✨በውስጡ ስለሚገኘው ሃሳብ (concept) በቀላሉ በመረዳት በአንድ ጊዜ ንባብ ለረጅም ጊዜ እንዲያስታውሰው ይረዳዋል።
3️⃣ሽምደዳን ሳይሆን ሃሳብን (concept) የተከተለ የትምህርት አሰጣጥ ፦ በርካታ ተማሪዎች ብዙ አንብበው ለመውደቃቸው ትልቁ ምክንያት የትምህርቶቹን ሃሳብ ባለመረዳታቸው ነው።
✨የኛ ትምህርቶች ሃሳብን ከማስጨበጥ አንፃር ባለፉት 2 አመታት ያስተማርናቸው ተማሪዎች ትልቅ ምስክር ናቸው።
4️⃣በቃል ለመያዝ ወይም ለመሸምደድ የሚያስችሉ መንገዶችን በመጠቀም ፦
ለምሳሌ፦ ባዮሎጂ ላይ የማትቀር የኦርጋኒዝሞች (organism) አመዳደብ አለች (ሁሌ ፈተና ላይ አትቀርም) ታዲያ ይህንን አመዳደብ ከትልቁ ወደ ትንሹ ሲቀመጥ Kingdom, Phylum, Class, Order, Family, genius , species ይሆናሉ።
✨ብዙ ተማሪዎች ይህን በቅደም ተከተል ለማስታወስ ይከብዳቸዋል ። ስለዚህ እኛ አንዳንድ ፊደል በመውሰድ ልዩ ቃል በመፍጠር በቅደም ተከተላቸው እንዲያስታውሱ አድርገናል። \“KPCOFGS\” (ኬፒሶፋገስ) በማለት። ይህንን የመሳሰሉ ልዩ የማስያዣ መንገዶች እንጠቀማለን።
5️⃣የትምህርቶቹ አፃፃፍ ፣ ስዕላዊ መግለጫዎች እና ሌሎችም በግራፊክስ እና በኤዲቲንግ ለማንበብ የሚመቹ እንዲሁም ለአይን የሚያምር ሆነው መዘጋጀታቸው የትምህርት አሰጣቱ ልዩ እና ተመራጭ ያደርገዋል።
🌟ተጨማሪ አገልግሎቶች
1. ለኢንትራንስ የሚያበቁ አስደሳች ቻሌንጆች
2.ሳምንታዊ የጥናት ፕሮግራሞችን
3.የ live ጥያቄ እና መልሶች
4.ምክሮችን እና ውይይቶችን
5.በነፃ የ5 አመት የኢንትራንስ ጥያቄዎችን ከነ ተብራራ መልሶቻቸው እና አሰራር ቴክኒኮች
‼️ማሳሰቢያ፦ ከ 1-5 የተቀመጡት አገልግሎቶች የሚጀመሩት ኢንትራንስ 3 ወር ሲቀረው ነው።