ዩኒቲ-ኮን.ካታሎግ ሰርቪስ | የግንባታ ሥራዎች እና ማቴሪያል ገበያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ(Addis Ababa, et)Trading Site🏗: post #284625 — TG.ME

የደረጃ 5 ጨረታ ምዝገባ ቅድመ ምዘና ዉጤት ማሳወቅን ይመለከታል::

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማዋን ነዋሪዎች የቤት ፍላጎት ለማሟላትና የከተማዋን እድገት ለማፋጠን በልዩ ትኩረት እየተገበረ ለሚገኘው መጠነ ሰፊ የቤት ልማት ፕሮግራም በግንባታው ዘርፍ የተሰማሩ እና አስፈላጊውን መስፈርት የሚያሟሉ በደንብ ቁጥር 199/2018 መሰረት ሥራ ተቋራጮችን ለመመዝገብ ከቅዳሜ 09/12/2018 ዓ.ም እስከ ሐሙስ 14/12/2018 ዓ.ም ድረስ ጥሪ ማድረጉና የምዝገባ ሂደቱ በስኬት መጠናቀቁ ይታወቃል።

በዚሁ መሠረት የቀረቡትን ሰነዶች የማጣራት ሥራ ተከናውኖ የመጀመሪያ ደረጃ የምዝገባ ሂደቱን ሙሉ በሙሉ ላሟላችሁ እና ስማችሁ ከዚህ በታች ለተዘረዘራችሁ ሥራ ተቋራጮች በሙሉ የቴክኒክ ሰነዳችሁን (Technical Proposal) በቴክኒክ ሰነዱ ላይ በተገለፀው የጊዜ ገደብ እና መስፈርት መሠረት እንድታስገቡ እናሳዉቃለን፡፡

ነሀሴ 15 ቀን 2018 ዓ/ም

የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን
ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት
@consite🏗
August 26, 2026 477 2