ለመውጫ ፈተና (Exit Exam) ቅሬታ አቅራቢዎች በሙሉ፤ የመውጫ ፈተና ውጤት ይፋ መደረጉን ተከትሎ፣ ውጤት… — UNITY UNIVERSITY REGISTRAR OFFICIAL — TG.ME

ለመውጫ ፈተና (Exit Exam) ቅሬታ አቅራቢዎች በሙሉ፤

የመውጫ ፈተና ውጤት ይፋ መደረጉን ተከትሎ፣ ውጤት ወይም ተያያዥ ቅሬታ ያላችሁ ተፈታኞች ቅሬታችሁን ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ቅሬታችሁን ለማቅረብ የሚከተሉትን መመሪያዎች በጥብቅ እንድትከተሉ እናሳስባለን፡-

• ቅሬታ ማቅረቢያ መንገድ፡ ውጤት ያያችሁበትን ሊንክ https://result.ethernet.edu.et/usernamepage በመጠቀም፣ በገጹ ላይ የሚገኘውን "Submit Complaint" የሚለውን አማራጭ በመጫን ማቅረብ ይቻላል።

• ቅሬታ የማቅረቢያ ጊዜ፡ ቅሬታ ማቅረብ የሚቻለው ከቀን 17/10/2018 እስከ 23/10/2018 ዓ.ም ድረስ ብቻ ነው።

ማሳሰቢያ፡ ቅሬታ አቅራቢዎች በአካል መምጣት የማይጠበቅባችሁ በመሆኑ፣ በኦንላይን ብቻ ቅሬታችሁን እንድታቀርቡ በአክብሮት እናሳውቃለን።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
❤20
June 23, 2026 23.4K 36