ተግባረዕድ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ለሹፌር መካኒክ ሰልጣኞች ሰርተፊኬት ሰጠ! ተግባረዕድ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ነሐሴ… — Addis Ababa Tegbareid Polytechnic College-Official Channel — TG.ME

ተግባረዕድ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ለሹፌር መካኒክ ሰልጣኞች ሰርተፊኬት ሰጠ!

ተግባረዕድ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን
ነሐሴ 25/2018 ዓ.ም


አዲስ አበባ ተግባረዕድ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በክረምት የአጫጭር ጊዜ ስልጠና መርሐ-ግብር በሹፌር መካኒክ ስልጠናቸውን በብቃት ላጠናቀቁ ሰልጣኞች ሰርተፊኬት አበረከተ።
ሰርተፊኬቱን የሰጡት የኮሌጁ የስልጠናና አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ዲን አቶ ደረሰ ጌታቸው፤ መሰል ስልጠናዎች ክህሎትን ለማሳደግና የራስን የሥራ ዕድል ለመፍጠር ትልቅ ፋይዳ እንዳላቸው ገልጸዋል። ኮሌጁ በአሁኑ ወቅት በሹፌር መካኒክ, Auto Mechanic & Electronics Maintenance, Home & Office Electronics Equipment Maintenance, Electrical Installation, CCTV Camera Maintenance, Fashion Design, Graphics Design, Computer Maintenance, Basic Computer, Furniture Making, Aluminum Works, Accounting  እና  ሌሎች የሙያ ዘርፎች ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ አዲስ ሰልጣኞችን እየመዘገበ መሆኑን  በማስተዋወቅ ያሉት ቦታዎች ውስን ስለሆኑ ፈጥነው እንዲመዘገቡ ጥሪ አቅርበዋል።

ለበለጠ መረጃ፡ 0909131406

ተግባረዕድ ኮሙኒኬሽንና ህዝብ ግንኙነት
👍2
August 31, 2026 3.6K 11