ግቢ ውስጥ አዲስ ሊሆኑባቹህ የሚችሉ የግቢ ቃላቶች ውስጥ ጥቂቶቹን እንመልከት! 🆕 ⭐️ ካፌ- ብዙሃኑ ተማሪ… — Temari News — TG.ME

🤔 ግቢ ውስጥ አዲስ ሊሆኑባቹህ የሚችሉ የግቢ ቃላቶች ውስጥ ጥቂቶቹን እንመልከት! 🆕

⭐️ ካፌ-  ብዙሃኑ ተማሪ የሚጠቀምበት  የግቢው መመገቢያ ቦታ

⭐️ ላውንጅ - ግቢ ውስጥ የሚገኝ ተማሪን ባመከለ መልኩ ክፍያ የሚያስፈልግ ካፌ ነገር ነው  ፤ ምግብና መጠጦቹ(ለስላሳ ፣ ትኩስ ነገር ምናምን) ጥራት ያላቸው እና በዋጋም በጣም ቅናሽ ናቸው።

⭐️ ችከላ- ጥናት

⭐️ ቴንሽን- ጭለላ ፣ ውጥረት፣ መረበሽ፣ መጨናነቅ

⭐️ 11  - ግማሽ እንጀራ በዳቦ ( የካፌ ምግብ ነው በተለይ እራት ላይ)

⭐️ Non-cafe - የግቢውን ካፌ የማይጠቀሙ ተማሪዎች

⭐️ Space - ባዶ ክፍል ብዙውን ጊዜ መማሪያ ክፍሎችን ለንባብ ስንጠቀምባቸው ስፔስ ይባላሉ

⭐️ Therefore- የካፌ ስጋ  ( ስጋ ሲባል ግን ሰፍ እንዳትሉ ! እንደስሙ ነው ማለት ትንሽ ስጋ ጣል ጣል የተደረገበት ገራሚ መረቅ )

⭐️ Cost -ካፌ ለማይጠቀሙ ተማሪዎች የሚሰጥ ወርሃዊ ክፍያ ፤ የሁሉም ማለት በሚቻል መልኩ ክፍያው ተመሳሳይ ነው።

⭐️ Add and drop - በትምህርት ሂደት ውስጥ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ነገሮች ናቸው ፤ ይሰውራቹህና የሆነ ኮርስ ከፈላ(F) add and drop process ግድ ይሆናል

⭐️ ድድ ማስጫ- አላፊ አግዳሚውን ለማየት አመቺ የሆነ ቦታ ወይም መቀመጫ 

⭐️ ዛፓ - ጥበቃ ሰራተኞች

⭐️ GC- ተመራቂ ተማሪዎች

⭐️ Fresh ፣ ጦጣ ምናምን  - አዲስ ገቢ ተማሪዎች ( ግቢ ስትገቡ ፍሬሽ ምናምን እያሉ አዛ የሚያደርጓቹህ ብዙውን ጊዜ ሁለተኛ አመቶች ናቸው ሁሉም ሁለተኛ አመቶች ሳይሆኑ ፍሬሽነታቸውን ያልጨረሱት ወይም ገራሚ ፉገራ የተፎገሩት ናቸው

⭐️ በርጮሎጂስት- የፍየልን መኖ የሚጋፉ ጫት ቃሚዎች ማለት ነው

⭐️ ኦቨር- መጠጥ ቤት መሄድና ሰክሮ መምጣት

⭐️ ጥፊ- የዶርምን ላይፍ እንዳይረሳ ከሚደርግ ግሩም ጠረኖች ውስጥ አንዱ ነው፤ በተለይ በተለይ ወንዶች ጋር የተለመደ የካልሲ ጭስ ነው ( ወንዶችዬ ተዉ ግን አታሰደቡን? )

⭐️ Meal Card- የግቢው ካፌ ውስጥ ለመመገብ በግቢው የሚሰጣችሁ የመመገቢያ ካርድ።


"... የማናውቃቸው ድብቅ ስሞች ካሉ Comment'ቱ ክፍት ነው 😅

📚ለትምህርት መፅሐፍት
💻 @Temari_Notes 💻 @Temari_Notes

📣ለትምህርታዊ መረጃዎች
💻 @TemariNews 💻 @TemariNews
❤41👍21😁20🔥2🙏1
September 5, 2026 13.2K 6 76