ሰባቱም ተማሪዎች ለአገልግሎቱ ማመልከት ስለሚገባቸው፣ ተማሪዎቹ ቅሬታቸውን እንዲያቀርቡ መረጃው እንዲደርሳቸው ጠይቋል፡፡
ተማሪዎቹ (3 የማኅበራዊ ሳይንስ እና 4 የተፈጥሮ ሳይንስ) ፈተናቸውን በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የፈተና ማዕከል የወሰዱ ናቸው።
(ጥር 11, 2022 የተከፈተና 18,853 ተከታዮች ያሉት የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር የቴሌግራም ገጽ ትናንት ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም ያጋራው መረጃ ከላይ ተያይዟል።)
በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ፈተናቸውን የወሰዱና ውጤታቸው Disqualified የተባለባቸው እጅግ በርካታ ተማሪዎች ቅሬታቸውን እያቀረቡ ይገኛሉ። በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የተገለፀው አይነት መሠል ግድፈት ሊኖር ስለሚችል ዩኒቨርሲቲዎች በድጋሜ የሪሚዲያል ተፈታኞችን ውጤት እንዲያዩ ይጠየቃሉ።




