የ ተዋህዶ ልጆች: post #9912 — TG.ME

ልባም ሴት ምን ዓይነት ናት?

፩. ልባም ሴት ራሷን ለፈጣሪዋ አሳልፋ ትሰጣለች።

፪. ልባም ሴት ለባሏ ዘውድ ነች በቤት ውስጥ እንደ እንደ አደይ አበባ ትታያለች የቤቱ ውበትም እርሷ ነች። ሁሉ ሲያት ይደሰትባታል ንግግሮችዋ በጨው የተቀመሙ ናቸው ተግባሯ የእውነተኛ ክርስቲያን ተግባር ነው።

፫. ልባም ሴት ለሐሜት ጊዜ የላትም ጊዜዋን በቃለ እግዚአብሔር፣ በጸሎት የተሞላ ነው፡፡

፬. ልባም ሴት ዓለም ላይ ያለው ልብስ ሁሉ ለሷ እንደማይመጥን ታውቃለች፤ በብልጭልጭ እና በፋሽን አትታለልም ሺህ ወንድ እሷን ፈልጎ ቢመጣ ምንም አይመስላትም ራሷን አታኮራም፣ ውበት ከንቱ ጠፊና ረጋፊ እንደሆነ ታውቃለችና።

፭. ልባም ሴት ሰውን አትንቅም ታጋሽ ነች ቁጣዋም የዘገዬ ነው፤ ለበጎ ሥራ እግሮችዋ ይሮጣሉ ንግግሯ ሁል በጨው እንደተቀመመ በቃለ እግዚአብሔር የታሸ ነው።

፯. ልባም ሴት ዕድሜዋን ሙሉ መልካም ታደርግለታለች፥ ክፉም አታደርግም።
(መፅሀፈ ምሳሌ 31 ፥ 12)

፯. ልባም ሴት ብዙ ተስፋ አላት በሚገጥማት ውጣ ውረድ አትጨነቅም ስጋትም አይገጥማትም እግዚአብሔር ከችግሮቿ በላይ ስለሆነ ችግሮችን እንደሚፈታ ታምናልች።

፰. ልባም ሴት ዝም ብላ በምድር ላይ ኖራ አታልፍም ለትውልድ የሚጠቅም ተግባር ሰጥታ ታልፋለች።

፱. ልባም ሴት ዓላማ እንደሌለው እንደ ኖህ አሞራ በወጣችበት አትቀርም፥ በጊዜ ወጥታ በጊዜ ትመለሳለች ፍሬ አልባ በለስም አይደለችም፥ በምታደርገው ነገር ሁሉ እንደ ንብ ታታሪ ነች።

፲. ልባም ሴት ከፈጣሪ የተሰጣት ጊዜ በአግባቡ ትጠቀማለች ያለ አግባቡ የሚባክን ጊዜና ሰዓት የላትም።

፲፩. ልባም ሴት ለማስታረቅ ትሮጣለች እንጂ በሰው ነገር አትገባም፤ ሰነፍ የተባለው ናባል ዳዊትን በሰደበው ጊዜ ዳዊትም ሊያጠፋው ሲሄድ ከመንገድ አቢጊያን አገኛት፥ እርሷም በትህትና ያዘችው ለመነችውም አሳቡንም አስቀየረች፥ ልባም ሴት መጥፎን በበጎ ታስቀይራለች።

፲፪. ልባም ሴት ቂም በቀልን አትይዝም ሆደ ሰፊና አርቆ አሳቢ ሁሉን እንደ አመሉ
የምታስተናግድ ትዕግስተኛ ናት።

በእውነት! "ልባም ሴት ማን ናት?"
( መፅሀፈ ምሳሌ 31 ፥ 10 - 30 ) በእርግጥም ልባም ሴት ዋጋዋ ከቀይ እንቁ ትበልጣለች። እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት ውበት ሽልማት ጌጥ ናት።



ሠናይ ቀን

💖
@Tekel_21 @Tekel_21
@Tekel_21 @Tekel_21
❤8🥰6😍4👍3
October 29, 2024 1.6K 3