#ሆያ_ሆዬ_ሆያ_ሆዬ
ሆያ ሆዬ ሆያ ሆዬ
ሆያ ሆዬ ሆያ ሆዬ (4)
ተገለፀ ሆ በታቦር ላይ ሆ
ብርሃኑን ሆ ለእኛ ሊያሳይ ሆ
የምሥራች ሆ እልል በሉ ሆ
ለሁሉ አባት ሆ ለ አዳኙ ሆ
በስምህም ደስ አላቸው ታቦር አርሞንዔም ብርሃን
ታየባቸው /4/
#አዝ___
ፅልመት ጠፍቶ ሆ ብርሐን ሆነ ሆ
በክርስቶስ ሆ ተከወነ ሆ
ያን ጨለማ ሆ በአንተ አልፈናል ሆ
በክርስቶስ ሆ ሰው ሆነናል ሆ
በስምህም ደስ አላቸው ታቦር አርሞንዔም ብርሃን
ታየባቸው /4/
#አዝ___
ጴጥሮስ ያዕቆብ ሆ ዮሐንስ ሆ
ሙሴ ኤልያስ ሆ በ ኢየሱስ ሆ
ተመርጠው ነው ሆ በዚህች እለት ሆ
ይህን ክብር ሆ ለማየት ሆ
በስምህም ደስ አላቸው ታቦር አርሞንዔም ብርሃን
ታየባቸው /4/
#አዝ
ለእኛ በዚህ ሆ ብንኖር ሆ
መልካም ነበር ሆ ያውም ክብር ሆ
ሦስት ዳስ ሆ እንስራና ሆ
እዚህ እንኑር ሆ በምሥጋና ሆ
በስምህም ደስ አላቸው ታቦር አርሞንዔም ብርሃን
ታየባቸው /4/
#አዝ___
ተገለፀ ሆ በታቦር ላይ ሆ
ብርሃኑን ሆ ለእኛ ሊያሳይ ሆ
የምሥራች ሆ እልል በሉ ሆ
ለሁሉ አባት ሆ ለ አዳኙ ሆ
በስምህም ደስ አላቸው ታቦር አርሞንዔም ብርሃን
ታየባቸው /4/
ዓመት ለዓመት ያድርሰን በእውነት /4/
ዓመት ለዓመት ያድርሰን በእውነት
ያድርሰን በህይወት ያድርሰን በህይወት/2/
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@Tekel_21 @Tekel_21
@Tekel_21 @Tekel_21
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯
5
4
4
3
2August 22, 2024 2.8K 4