አደራ...
ምን እንደጎደለኝ ሳልነግርሽ ታውቂያለሽ
ከማንም በላቀ ታስፈልጊኛለሽ። መቋጠሪያው ጠፍቶ የጭንቀቴ ውሉ
ድንግዝግዝ ብሎ ይታየኛል ሁሉ።
በእቅፍሽ ያቀፍሽው የሰላሙ አለቃ ፍቅር አለ በእጁ ለአለም የሚበቃ።
እንደ ዶኪማስ ቤት ጎጆዬን ደግፊ
ልጄ ሆይ በይና ልቤን አሳርፊ።
የነፍሴንስ ነገር አደራ እመቤቴ
በምልጃሽ ይሰራ የዘላለም ቤቴ።
@Tekel_21
@Tekel_21
@Tekel_21
@Tekel_21
6
2July 12, 2024 1.7K 6