የ ተዋህዶ ልጆች: post #8099 — TG.ME

🌹❖ቅዱስ ገብርኤል ማን ነው🌹

✥##ገብርኤል ማለት " እግዚእ ወገብር”፦ የእግአብሔር አገልጋይ ማለት ነው። ፍጥረታት መፈጠር በጀመሩበት በዕለተ እሑድ እግዚአብሔር መላእክትን ከፈጠራቸው በኋላ ተሰወራቸው መላእክትም “መኑ ፈጠረነ፦ማን ፈጠረን” ሲሉ ዲያብሎስ እኔ ፈጠርኳችሁ ብሎ መላእክት በተረበሹ ጊዜ “የፈጠረንን✥አምላካችን እስክናውቅ በያለንበት ጸንተን እንቁም” ብሎ ያረጋጋቸው መልአክ ነው። በዚህም ምክንያት ጌታ “በእንተዝ ይደልዎ ከመ ይጹር ዜናሃ ለማርያም” እንዲል ሥጋዌውን ለድንግል እንዲያበስር አድሎታል።

✥ይህ ቅዱስ ገብርኤል ነው✥
ሰጥናኤል ሥላሴን በካደ ጊዜ መላእክትን በቃሉ ያጽናናቸው

✥ይህ ገብርኤል ነው✥
ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱና በእግዚአብሔር ፊት የሚቆም

✥ይህ ገብርኤል ነው✥
በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ ለሚኖሩ ብርሃን የገለጸና የሰበከ ይህ

✥ቅዱስ ገብርኤል ነው✥
የነቢያትን ትንቢት የፈጸመ፤የክርስቶስን ልደት ለድንግል ያበሰረ

✥ቅዱስ ገብርኤል ነው✥
ዳንኤልን ከአናብስት ያዳነው

✥ይህ ገብርኤል ነው✥
ሠለስቱ ደቂቅን ከእቶን እሳት ያዳነቸው

✥ይህ ገብርኤል ነው✥
ወደ ዘካርያስ የተላከ የዮሐንስን ልደት ያበሰረ

✥ይህ ገብርኤል ነው✥
ወደ ዮሴፍና ወደ ኒቆዲሞስ የተላከ

✥ቅዱስ ገብርኤል ነው✥
ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣን ከእቶን እሳት ያዳናቸው

✥ይህ ገብርኤል ነው✥
ሰብአ ሰገልን በኮከብ ምልክት የመራቸው

✥ይህ ገብርኤል ነው✥
ድንግል ማርያምና ሕፃኑን ክርስቶስን በምድረ በዳ በስደታቸው የመራ

✥ይህ ገብርኤል ነው✥
የብርሃን ራስ ወርቅ የተቀዳጀ

✥ገብርኤል ነው✥
የአሸናፊና የኃይል መልአክ

✥ገብርኤል ነው✥
ነበልባላዊ ዖፈ ሰማይ

✥ገብርኤል ነው✥
"የመልአኩ ጥበቃ እና ረድኤት አይለየን"
❖አሜን❖


@Tekel_21
@Tekel_21
@Tekel_21
@Tekel_21
👍1
July 4, 2024 1.6K 9