55ቱ የሕይወት መርሖች በአባ ቶማስ ሆፕኮ (የምስራቅ ኦርቶዶክስ አባት)
1. ሁልጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሁን።
2. እንደምትፈልገው ሳይሆን እንደምትችለው መጠን ጸልይ::
3. በአግባቡ የምታከብረው ጥብቅ የጸሎት ሥርዓት ይኑርህ።
4. የጌታን ፀሎት( ዘበሰማያትን) በቀን ውስጥ በተደጋጋሚ ጸልይ።
5. አእምሮህ ከሌሎች ጉዳዮች ነጻ በሚሆንበት ሰዓት የምትጸልየው አጭር ጸሎት ይኑርህ።(ጌታዬ ኢየሱስ ከርስቶስ ሆይ እኔን ኃጢያተኛውን ማረኝ)
6. በጸሎትህ ላይ ስግደትን አክልበት።
7. ሰውነትህን የማይጎዱ መልካም ምግቦችን በመጠኑ ተመገብ።
8. የቤተከርስቲያንን የአጽዋማት ሥርዓት አክብር።
9. በቀንህ ውስጥ የአርምሞ ጊዜ ይኑርህ።
10. የልግስና ሥራህን በድብቅ አከናውን።
11. መደበኛ የቅዳሴ ጊዜ ይኑርህ::
12. በንስሐ ሕይወት ተመላለስ፤ ሥጋ ወደሙንም በቋሚነትና በመደበኛነት ተቀበል።
13. ጎጂና የማይጠቅሙ ሀሳቦች በአእምሮህ እንዲመላለሱ አትፍቀድ፧ ገና ከጅምሩ ቆርጠህ ጣላቸው ::
14. ሀሳብህንና ስሜቶችህን ሁሉ ለምታምነው ሰው በየጊዜው ግለጥ።
15. መጽሐፍ ቅዱስን በየዕለቱ (በየጊዜው)አንብብ።
16. ጥሩ መጻሕፍትን በመጠኑ አንብብ፡፡
17. ከቅዱሳን ጋር ኅብረትን አዳብር።
18. ተራ ሰው ሁን።
19. ለሁሉም ሰው ጨዋና ትሑት ሁን።
20. የቤትህን ንጽሕና እና ሥርዓት ጠብቅ።
21. በትርፍ ጊዜ የምትሰራው ጤናማ(በጎ) ሥራ ይኑርህ::
22. በየጊዜው የአካል እንቅስቃሴን አድርግ::
23. የዕለት ኑሮህን ኑር።
24. ታማኝ ሁን፧ በመጀመሪያ ግን ለራስህ ታመን።
25. በጥቃቅን ነገሮች እንኳ ታመን፡፡
26. መሥራት የሚገባህን /ያለብህን/ ሥራ፧ ከዚያም እርሳው::
27.. ከባድና አስቸጋሪ ነገሮችን ቀድመህ ሥራ።
28. እውነታውን ተጋፈጥ።
29. በሁሉ ነገር አመስግን።
30. ደስተኛ ሁን።
31. ተራ፣ ድብቅ (ልታይ የማትል)፣ ዝምተኛና ታናሽ ሰው ሁን።
32. ወደ ራስህ ትኩረትን ፈጽሞ አትሳብ።
33. ሰዎች ሲያናግሩህ አድምጣቸው::
34. ነገሮችን በንቃት ተከታተል።
35. ከሚያስፈልጉህ ነገሮች ውጪ አታስብ፤ አትናገርም።
36. ስታወራ በቀላሉ፧ በግልጽ፧ በአጽንዖት እና በቀጥታ አውራ።
37. ነገሮችን ከማለም፣ ከማሰላሰል ከምኞት ራቅ፡፡
38. ሥጋዊና ፍትወታዊ ነገሮችን ከጅምሩ ሽሻቸው::
39. አታጉረምርም/አትነጫነጭ።
40. ከሌላ ከማንም ጋር ራስህን አታወዳድር።
41. ከማንም ክብርንም ሐዘኔታንም አትፈልግ፤ አትጠብቅ።
42. በማንም ላይ በማናቸውም ሁኔታ አትፍረድ::
43. ሰዎችን በምንም ነገር ላይ ለማሳመን አትሞከር።
44. ራስህን አትከላከል ወይም ትክክለኛነትህን ለሌሎች ለማረጋገጥ አትሞከር።
45. በእግዚአብሔር ብቻ ታወቅ/ተከበር።
46. ትችትን በክብር ተቀበል ግን በሚገባ ፈትነው::
47. ሰዎችን መምከር አስፈላጊ ሲሆንና ሲጠይቁህ ብቻ ምከር።
48. በራሳቸው ማድረግ ለሚገባቸውና ማድረግ ለሚችሉ ሰዎች ምንም አታድርግ።
49. ቀንህን በእቅድ ምራው፧ ድንገት በሚመጡልህ ሃሳቦች ብቻ የቀን ውሎህን አትምራ።
50. ለራስህና ለሌሎች ምሕረትን አድርግ።
51. እስከመጨረሻው እስትንፋስህ ድረስ በጽኑ ከመፈተን ውጭ ሌላ ምንም ነገር በሕይወትህ ውስጥ አትጠብቅ፡፡
52. በጌታና በብርሃን ላይ አንጂ በኃጢአትና በጨለማ ላይ አታተኩር።
53. የእግዚአብሔር ቸርነቱ ከመተላለፍህ በላይ ነውና ራስህን በጸጸት ብዛት አትጉዳ፧ ተስፋም አትቁረጥ።
54. ስትወድቅ በፍጥነት ተነሥ፧ እንደገናም ጀምር።
55. እርዳታ በሚያስፈልግህ ጊዜ ያለ ሐፍረትና ፍርሃት ጠይቅ፡፡
@Tekel_21
@Tekel_21
@Tekel_21
@Tekel_21
1July 4, 2024 840 4