የአዲስ አበባ አሽከርካሪና ተሽከርካሪባለሥልጣን # ከመጋቢት_24_2017_ጀምሮ_… — Teddy 2 Driving School — TG.ME

የአዲስ አበባ አሽከርካሪና ተሽከርካሪባለሥልጣን # ከመጋቢት_24_2017_ጀምሮ_ የመንጃ_ፈቃድ_ዕድሳት_አገልግሎት_በየአቅራቢያው_በመታወቂያ_አድራሻ_ሳይገደብ_እንዲሰጥ_ተፈቀደ! የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላትን እንደገና ለማቋቋም በወጣው አዋጅ ቁጥር 84/2016 የተዋቀረው የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን በሁለት ዘርፍ ከ55 በላይ ዋና ዋና አገልግሎቶችን ይሰጣል። በዚህ አግባብ የአሽከርካሪ ዘርፍ ከተሰጠው ሥልጣን እና ተግባር ውስጥ ብቁ አሽከርካሪ ማፍራት ዋናው ተልዕኮው ነው። ተቋማችን በሪፎርም ሂደት ውስጥ የሚገኝ እንደመሆኑ፤ ህዝባችን በዘርፉ ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኝ በርካታ አሰራሮችን በማሻሻል የተገልጋይ ዕርካታን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ጥረት እና ለውጥ እየተደረገ ነው። በ2017 በጀት ዓመት ከለየናቸው ለዓመታት የከረሙ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ውስጥ አንዱ በመታወቂያ አድራሻ ሳይገደብ በአቅራቢያ መንጃ ፈቃድ የማደስ ጥያቄ ይገኝበታል። በተቋማችን የአሽከርካሪ አገልግሎት የሚሰጥበት ሲስተም የተማከለና አስተማማኝ እንዲሆን ቀድሞ ሰፋፊ የማሻሻያ ተግባራት መሰራታቸውን በማረጋገጥ፤ የተቋሙ ስትራቴጅክ ማኔጅመንት ከመጋቢት 24፣ 2017 ዓ.ም ጀምሮ ተገልጋዮቻችን በሚቀርባቸው ቅርንጫፍ ፋይላቸው ያለበት ቅርንጫፍ ሳይጠየቅ የጤና ምርመራ ሰርተፍኬትን በመያዝ የመንጃ ፈቃድ ዕድሳት አገልግሎት እንዲያገኙ ተወስኗል። በቀጣይም ተቋሙ በዘርፉ የተገልጋይ ዕርካታ በመጨመር፣ የህዝብ አመኔታ የሚጣልበት እስኪሆን ድረስ በትጋት የሚሰራ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን።

April 1, 2025 2.2K 4