❤️ክብር እና ምስጋና ለመምህራን ይሁን!❤️ ▶️ ወቅታዊ ሁኔታዎችን ገምግመን ለ2 ሳምንታት እረፍት አድርገን ተመልሰናል፡፡ ▶️ ስኬት እንዲሁ ሮጦ ሄዶ መድረስ ማለት አይደለም፣ መስራት የሚገባንን ሰርተን እና ጠልፈው ሊጥሉን የሚችሉ ነገሮችን ጭምር ማለፍ ነው፡፡ ▶️ ከያዝነው አላማ አንፃር ብዙ ተግዳሮቶች እንደሚገጥሙን አስበንበት ነው የገባነው፣ አልጋ ባልጋ የሆነ ነገር መጠበቅ የለብንም፡፡ ▶️ አሁን እንደ በፊቱ 3 ብቻ አይደለንም፣ ብዙ ወንድሞቻችን ከጎናችን ሆነው እያገዙን ነው፡፡ ▶️ ግንዛቤ ለመፍጠር የሄድንበት መንገድ ቀላል የሚባል አይደለም፣ በአለን መረጃ መሰረት ከ40ሺህ በላይ የዩኒቨርሲቲ መምሀራን እና ከ200 ሺህ በላይ የመደበኛ መምህራን ግንዛቤው አላቸው፣ ግን በቂ አይደለም፡፡፡፡ ▶️ እኛ ስራውን ሰርተን መጨረስ አላቃተንም፣ የምንጠብቀው 1ኛ የዩኒቨርሲቲ መምህራንን ነው፣ 2ኛ ደግሞ ምቹ ሁኔታ ነው፡፡ ግንዛቤ መፍጠር ላይ ብዙ ስራ አልሰራንም፣ በተለይ ደግሞ በየትምህርት ቤቱ ዘመቻ አድረገን አልቀሰቀስንም፡፡ ስለዚህ አሁንም ብዙ ስራዎች ይጠብቁናል፡፡ እኛ ከጊዜ ጋር ጠብ የለንም ፣ አላማችን ለማሳካት የቻልነውን ሁሉ እያደርግን ነው፡፡ ▶️▶️ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ አዲስ ነገር ይኖረናል፡፡ ▶️▶️ የመምህራን ባንክ እውን ይሆናል፡፡ የመምህራን ባንክ ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ
ክብር እና ምስጋና ለመምህራን ይሁን!❤️ ▶️ ወቅታዊ ሁኔታዎችን ገምግመን ለ2 ሳምንታት እረፍት አድርገን… — Teachers' Bank/የመምህራን ባንክ — TG.ME
December 24, 2022 3.3K 3 1