ክብር እና ምስጋና ለመምህራን ይሁን! አብዛኛው መምህራን በተለያየ ጊዜ contact ውስጥ ያሉትን መምህራን add/invite አድርገዋል፣ ከልብ እናመሰግናለን፡፡ እባካቹህ አዲስ ወደ ግሩፑ የተቀላቀላቹህ መምህራን በምትሰሩበት ተቋም እና ስልካቹህ ውስጥ ያሉትን መምህራን ወደ ግሩፑ በመጋበዝ የድርሻቹህን ተወጡ፣ በተለይ ደግሞ ክፍለ ሀገር የምንሰራ መምህራን፡፡ እኛ እያሳለፍነው ካለነው ውጣ ውርድ እና መስዋትናት ጋር ሲወዳደር ግንዛቤ መፍጠር እና ወደ ግሩፖ add/invite ማድረግ እኮ ትንሿ ስራ ናት:: እያንዳንዷ አስተዋፅኦ ዋጋ አላት፣ ብንሰራ ውጤታማ እንሆናለን፣ ከተሳካ የሁላችንም አሻራ ስላለ ደስተኛ አንሆናለን፣ ባይሳካ ደግሞ የምንችላውን ስላደረግን ቁጭት ውስጥ አንገባም፣ ጠቢብ ባንከን እውን ለማድረግ የሁሉንም መምህራን ቅንነት እና ቁርጠኝነት ይጠይቃል፣ በጣም የሚገርመው በራሳችን ተነሳሽነት መስራት ሲገባን በየጊዜው መለመን እና መወትወት መፈለጋችን ትዝብትን ይጭራል፡፡ ብዙዎች ለእኛ የሚሰሩ መስሎ ይታያቸዋል፣ የምንሰራው ለራሳችን ለመምህራን ነው፡፡ ጠቢብ ባንክ የሞት-ሽረት ጉዳያችን ነው፣ ባንክ ብቻ አይደለም!!!! ሁላችንም ወደ ስራ እንግባ!!! ሁለት ጥየቄዎችን ልጠይቅ፡- 1ኛ፡- ስንት መምህራንን ወደ ግሩፑ ጋበዝን? 2ኛ፡- ስንቶቻችን ሊንኮችን በማህበራዊ ሚዲያዎች አጋራን? https://t.me/teacher_Bank https://t.me/Teachers_bank_chat መልካም ቀን! አዎ መምህር ነኝ!
TelegramTeachers' Bank/የመምህራን ባንክዋና አላማዎች፡- ✔️ የት/ት ጥራትን ለማሻሻል የመምህራንን የኑሮ ሁኔታ መሻሻል፡፡ ✔️ የመምህራንን ኑሮ በዘላቂነት ሊለውጡ እና የት/ት ሴክተሩን ሊደገፉ የሚችሉ የኢኮኖሚ አውታሮችን መዘርጋት ፡፡ ዝርዝር አላማዎች፡- 1. የመምህራን ባንክ ማቋቋም፣ 2. የትምህርት ሚዲያዎችን ማቋ…ክብር እና ምስጋና ለመምህራን ይሁን! አብዛኛው መምህራን በተለያየ ጊዜ contact ውስጥ ያሉትን መምህራን… — Teachers' Bank/የመምህራን ባንክ — TG.ME
November 20, 2022 4.1K 6