⏰⏰⏰⏰ ክብር እና ምስጋና ለመምህራን ይሁን! ከጎናቹህ ነን! በርቱ! ደስተኛ ነን! እናመስግናለን! የመምህራን ፀሀይ ልትወጣ ነው! የሚሉ ቃላቶችን ስትፅፉ እኛም ታላቅ መነሳሳትን እየፈጠረልን እዚህ ታላቅ ደረጃ ላይ ደርሰናል፡፡ ብዙዎቻቹህም በኮሚቴ እና ባስተባባሪ ደረጃ ተመዝግባቹህም ሆነ መምህር በመሆናቹህ ብቻ ከጎናችን ተሰልፋቹህ ሕጋዊ ሂደቱን ለማጠናቀቅ የምትመክሩን፣ የምታበረታቱን እና ወደ ግሩፖ መምህራንን add/invite በማድረግም ሆነ በስራ ቦታቹህ ግንዘቤ በመፍጠር ለምታግዙን በርካታ መምህራን ከልብ የመነጨ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ ሕጋዊ ሂደቱን ለማስጨረስ ብዙ ውጣ ውረዶች አሉት፡- የዶክሜንት ዝግጅት፣ ታላላቅ ሰዎችን እና ባለሞያዎችን ማማከር፣ ልምድ መቅሰም፣ የጉዳይ ማስፈፀሚያ ብር ማስባሰብ እና ጉዳይ ማስፈፀም የእለት ከእለት ተግባሮቻችን ናቸው፡፡ በተጨማሪም መምህር አንደመሆናችን መጠን እንደእናንተ የማስተማር ስራ ጫና አለብን፡፡ እኛ ይህን ጫና ሁሉ ተሸክመን ሳንጎብጥ፣ ሳንሰለች፣ ምን አገባኝ ሳንል፤ በአብዛኛው የመምህራን ክፍል ግን መሰላቸቶችን፣ ምን አገባኝ በሚል ዳር ላይ ቆሞ ማየትን የመረጥን ብዙ አንደሆንን ከድርጊታችን ማየቱ በቂ ነው፡፡ ይህም አፍራሽ ነገሮችን በመፃፍ፣ ወሬ ብቻ! ተጓተተ! ዘገያቹህ! ምንም የሚታይ ነገር እየሰራቹህ አይደለም! የተለያየ እና የሚምታቱ ሀሳቦችን እያቀረባቹህ ነው! በሚሉ ድርጊቶች ይገለፃሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ስንቶቻችን በሚቀርቡ የውይይት ሀሳቦች ላይ የራሳቸን ሃሳብ ግባት በመስጠት እንሳተፋለን፣ በአብዛኛው ሳምንት ቆይተን ገብተን እንደአዲስ ሀሳብ እናነሳለን፣ የመምህራን ባንክን ለመመስረት የሚደረገው እንቅስቃሴ የትርፍ ጊዜ (pertime) ስራ አይደለም፣ ሁላችንም ሙሉ ጊዜ (full time) ሰጥተን በየእለቱ እየተከታተልን የምናሳካው የሞት-ሽረት ጉዳያቸን ነው፡፡ ከ160 በላይ አስተባባሪዎች ተመዝግበዋል፣ እኛ በሕጋዊ ሒደቱ ተጠምደን፣ የማስተባበሩን ስራ ወደ እናንተ በማስተላለፍ ላይ ብንሆንም ከምዝገባ ያለፈ እንቅስቃሴዎች አይታዩም፣ የመሰላቸት እና የመቀዛቀዝ ባህሪየት እየተስታዋሉ ናቸው፡፡ በእርግጥ ግልፅ የሆነ የስራ ድርሻ አልሰጠነም፡፡ እባካቹህ ውድ መምህራን የጀመርነው የባንክ ሒደት ግዙፍ እና አገር አቀፍ ፕሮጀክት በመሆኑ እና በአስተባባሪዎች ጥረት ብቻ ከግብ የማይደርስ መሆኑን ተገንዝባቹህ በያላቹህበት ሆናቹህ የሚጠበቅባቹህን ግንዛቤ የመፍጠር እና ወደ ግሩፖ መምህራንን add/invite የማድረግ ስራን አንደታግዙን በመላው መምህራን ስም ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡ ✅ ጠቢብ ባንክ በምስረታ ላይ መሆኑን ግንዛቤ አንፍጠር፣ ✅ መምህራንን ብቻ ወደ ግሩፖ add/invite እናድርግ ✅ በዚህ ሳምንት 25ሺህ አባላት በማድረስ ከጎናችን መሆናቹህን አሳዩን! ↩️ ሕጋዊ ሆነን በቲቪ እና በጋዜጣ ማስነገር እስክንጀምር ድረስ ያሉን አማራጮች የማህበራዊ ሚዲያዎች ናቸው፡፡ ሊንኮችን እናጋራ፡- https://t.me/teacher_Bank https://t.me/Teachers_bank_chat የመምህራን ባንክ ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ
TelegramTeachers' Bank/የመምህራን ባንክዋና አላማዎች፡- ✔️ የት/ት ጥራትን ለማሻሻል የመምህራንን የኑሮ ሁኔታ መሻሻል፡፡ ✔️ የመምህራንን ኑሮ በዘላቂነት ሊለውጡ እና የት/ት ሴክተሩን ሊደገፉ የሚችሉ የኢኮኖሚ አውታሮችን መዘርጋት ፡፡ ዝርዝር አላማዎች፡- 1. የመምህራን ባንክ ማቋቋም፣ 2. የትምህርት ሚዲያዎችን ማቋ…ክብር እና ምስጋና ለመምህራን ይሁን! ከጎናቹህ ነን! በርቱ! ደስተኛ ነን! እናመስግናለን! የመምህራን ፀሀይ… — Teachers' Bank/የመምህራን ባንክ — TG.ME
November 18, 2022 3K 3