ክብር እና ምስጋና ለመምህራን ይሁን! ጠቢብ ባንክን ለመመስረት በሚደረገው ሒደት ውስጥ አደራጅ ወይም… — Teachers' Bank/የመምህራን ባንክ — TG.ME

ክብር እና ምስጋና ለመምህራን ይሁን! ጠቢብ ባንክን ለመመስረት በሚደረገው ሒደት ውስጥ አደራጅ ወይም አስተባባሪ ለመሆን እና ስራ ለማገዝ ባወጣነው ጥሪ መስረት እስካሁን 147 መምህራን ይተመዘገቡ ሲሆን፣ ጥሪያችን ተቀብላቹህ ለተመዘገባቹህ መምህራን ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ በአዲስ አበባ በቂ አስተባበሪ መምህራን የተመዘገቡ ሲሆን ክፍለ ሀገር፣ በግል ትምህርት ቤቶች፣ በግል ኮሌጆች፣ ዩኒቨርሲቲዎች፣ እና ኮሌጆች የምትሰሩ በድጋሚ በሚከተለው ቡት እየገባቹህ እድትመዘገቡ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡ https://t.me/Tebibbank_bot ስትመዘገቡ፡- ✍️ ሙሉ ስም …..................... ✍️ የሰራ አድራሻ …..................... ✍️ስልክ ቁጥር …..................... ✍️የምትሰጡት የሞያ እርዳታ /አገልግሎት/ ….................. ማሳሰቢያ፡- 1ኛ፡- ስልክ ከመደወል በተጨማሪ ከአስተባሪ አባላት ጋር ብቻ የምንገናኝበት የቴሌግራም ግሩፕ የምንከፍት ይሆናል፡፡ 2ኛ፡- ከመላው መምህራን ጋር የonline ስብሰባ በGoogle meet የምናዘጋጅ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ 3ኛ፡- ከመጀመሪያው ጀምሮ ከአሁን በፊት የተመዘገባቹህ ድጋሚ አትመዝገቡ፣ ሰም ዝርዝራቹህ ስላለን፡፡ ነሐሴ ወር ላይ ለስብሰባ የተመዘገባቹህትን ይጨምራል፡፡ የመምህራን ባንክ (ጠቢብ ባንክ) ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ

November 12, 2022 3.6K 1 1