ክብር እና ምስጋና ለመምህራን ይሁን! ጠቅለል ባለ መልኩ ፡ - በጣም ጥንቃቄ ማድረግ ያለብን እና የጥንቃቄ… — Teachers' Bank/የመምህራን ባንክ — TG.ME

ክብር እና ምስጋና ለመምህራን ይሁን!

ጠቅለል ባለ መልኩ ፡ - በጣም ጥንቃቄ ማድረግ ያለብን እና የጥንቃቄ መልክቶች፡፡

1ኛ፡- መምህራንን በተመለከተ የምንሰራቸው ስራዎች ሁሉ በኢትዮጵያ የሚገኙ ሁሉንም መምህራን የሚመለከቱ በመሆናቸው አይመለከተኝም የሚል እሳቤ በጭራሽ ሊኖር አይገባም፣ አይመለከተኝም ብለን እጃችን አጣጥፈን የምንቀመጥበት ጊዜ ላይ አይደለንም፣ አመናቹህም አለመናቹህም መጭው ጊዜ ለመምህራን የባሰ ጨለማ ነው፡፡

2ኛ፡- የምንሰራው ቢዝነስ መሆኑን ተገንዝበን የመንግስት ህግን አክብረን እና የትምህርት ባለድርሻ አካላትን መብት ሳንነካ ያቀድነውን ለማሳካት የሚያግደን ምንም ነገር እንደሌለ መገንዘብ አለብን፣

3ኛ፡- የመምህራንን ችግሮች እና የኢኮኖሚ ጥያቄዎች ለመፍታት እስከሰራን ድረስ አግባብነት ያላቸውን ጥያቄዎች ሁሉ የመመለስ ግዴታ አለብን፣ መነቃቀፍ እና የሌሎችን ሀሳቦች ማጣጣል ከኛ አይጠበቅም፣ ምሁር ያዳምጣል አንጅ ለመናገር አይጣደፍም፣ ከመፃፋችን በፊት የሚያመጣውን በጎ-ጎን ወይም መጥፎ አጋጣሚ መፈተሸ አለብን፡፡ የግል ፍለጎታችን ሳይሆን የሁሉንም መምህራን ጥቅም እናስብ!!

4ኛ፡- የእኛን ጉዳይ ሌላ አካል ያሳካልናል ብላቹህ አንዳትጠብቁ፣ የእኛን እድል የምንወስነው እኛ ብቻ ነን፣ የእኛ አንድነት እና ተደራጅተን እራሳችን በኢኮኖሚ እስካልቀየርን ድረስ ላለፉት 3 አስርት አመታት የተደገሰልንን እየበላን አንቀጥላለን!!!

5ኛ፡- እኛን ለማፈራረስ ብዙ ስራዎች እየተሰሩ አንደሆነ እያየን ነው፣ ብዙ ሙከራዎችም ተደርገዋል፣ ግን አይሳካም፡፡ ከኛ የሚጠበቀው በአንድ ላይ ቆመን፣ ክፍተቶችን ሁሉ ዘግተን መንቀሳቀስ አለብን፣ ሳታውቁ ወይም ሳይገባቹህ አሉታዊ ነገሮችን የምትፅፉ ከዚህ ድርጊታቹህ አንድትታቀቡ እናሳስባለን፣

6ኛ፡- እዚህ ቻት ግሩፕ ላይ የምንሰራው ስራ ለማንቂያ እና ግንዛቤ ለመፍጠር ያክል እንጅ የምንሰራውን ስራ ሁሉ እዚህ ላይ የመዘክዘክ ግዴታ የለብንም፣ ቢዝነስ አኮ ሚስጢር ነው፡፡ የትኛው ባንክ ነው ሒደቱን እየዘከዘከ የተመሰረተው፣ ወይስ ንገሩን እና እናፍርሳቹህ ለማለት ነው፡፡ እኛ ስራችን አንድ ደረጃ ከፍ አድርገን እየሰራን ነው፣ ፍፃሜው ላይ እንገናኝ፡፡

7ኛ፡- ብስለት የተሞላበት አካሄድ መሄድ አለብን፡፡ የማይጠቅመን እና ጉንጭ አልፋ ልዩነቶችን እያመጣን ጊዜ ማጥፋት የለብንም፡፡ ይህ ትውልድ ከምንቀርፀው መምህራን አይጠበቅም፣ አርአያ መሆን አለብን፣ ከመምህራን ስነ-ምግባር ጋር አብሮ አይሄድም፡፡

አዎ መምህር ነኝ!
👍10❤3
November 11, 2022 3K 1