🌷አሏህ ለኛ እጅግ በጣም ያዝናል
ዑመር ቢን አል-ኸጣብ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ አሉ:-
قَدِمَ رسول الله ﷺ بسبي
ወደ አላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ምርኮኞች ቀረቡ።
فإذا امرأة من السبي تسعى
ከምርኮኞቹ መካከል አንዲት ሴት (ልጇን ፍለጋ) ትሯሯጥ ነበር።
إذْ وجدت صبيًّا في السبي أخذته فألزقته ببطنها فأرضعته
በምርኮው ውስጥ አንድ ሕፃን ልጅ ስታገኝ (ወዲያው) አንስታ ከሆዷ ጋር አጣበቀችው፣ ከዚያም አጠባችው።
فقال رسول الله ﷺ: أترون هذه المرأة طارحةً ولدها في النار؟
የአላህ መልእክተኛም (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ:- «ይቺን ሴት ልጅዋን በእሳት ውስጥ ትጥላለች ብላችሁ ታስባላችሁ?»
قلنا: لا والله
እኛም «አይ፣ በአላህ (አትጥልም)» አልን።
!فقال: الله أرحم بعباده من هذه بولدها
እሳቸውም (ሰ.ዐ.ወ) «አላህ ለባሮቹ ካለው ራሕመት (ምሕረት)፣ ይህች እናት ለልጇ ካላት ራሕመት እጅግ በጣም አዛኝ ነው» አሉ።
August 31, 2026 18