Are you afraid of starting to post? የይዘት ፈጠራ (Content Creation) ለመጀመር… — Sufi Learn — TG.ME

Are you afraid of starting to post? የይዘት ፈጠራ (Content Creation) ለመጀመር እያሰቡ ነው? ነገር ግን 'ካሜራ የለኝም'፣ 'የሚያምር ስቱዲዮ የለኝም' ወይም 'ሰዎች ምን ይሉኛል?' ብለው እየፈሩ ከሆነ፣ እስኪ እውነቱን ልንገራችሁ... አሁኑኑ ላለመጀመር ምንም አይነት ምክንያት የላችሁም! ብዙዎቻችን የይዘት ፈጠራ ሲባል ትልቅና ውድ እቃዎች የሚያስፈልጉ ይመስለናል፤ ግን ትልቁ ሚስጥር እሱ ሳይሆን አሁን በእጃችሁ ያለው ስልክ ብቻ ነው። ስልክ ካላችሁ መቅረጽ፣ መጻፍና መቅዳት ትችላላችሁ፤ እንዲሁም የግድ የሁሉም ነገር አዋቂ መሆን ሳይጠበቅባችሁ የምትወዱትን ነገር፣ የምታውቁትን የሙያ መስክ ወይም የእለት ተእለት ህይወታችሁን በማጋራት በቀን በ30 ደቂቃ ብቻ ትልቅ ለውጥ ማምጣት ትችላላችሁ። ቪዲዮ፣ ጽሁፍ፣ ድምፅ እና ምስልን በመጠቀም ሀሳባችሁን ለዓለም ማጋራት የምትችሉበት ዕድል እጃችሁ ላይ ስላለ፣ ፍጹም የሆነ ቀን ወይም እቃ ሳትጠብቁ ዛሬውኑ የመጀመሪያውን እርምጃ እንድትወስዱ እጋብዛችኋለሁ ይህንን ጉዞ አብረን ለመቀጠልም ገጼን ፎሎው እና ሰብስክራይብ ማድረግ እንዳትረሱ

June 16, 2026 8