በአዲስ አበባ ከተማ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ተፈታኞች ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ መግባት ጀመሩ አዲስ… — St.Raguel Secondary School — TG.ME

በአዲስ አበባ ከተማ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ተፈታኞች ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ መግባት ጀመሩ አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በከተማ አስተዳደሩ የ2016 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች ፈተናውን ወደሚወስዱባቸው ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግባት ጀመሩ። ከሐምሌ 3 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮም የማኅበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ፈተናቸውን እንደሚወስዱ ተገልጿል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) እና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ተፈታኝ ተማሪዎች ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ፣ አራት ኪሎ፣ ኤፍቢኢ እና አምስት ኪሎ ካምፓሶች ሲገቡ አበረታትተዋል፡፡

July 8, 2024 2.2K 1