በምድር ላይ ሆኖ ዘለዓለማዊ ዋጋ ያለውን ሥራ መሥራት ይቻላል! በምድር ላይ ሆኖ ዘለዓለማዊ ዋጋ ያለው ሥራ… — Joy online market — TG.ME

📌 በምድር ላይ ሆኖ ዘለዓለማዊ ዋጋ ያለውን ሥራ መሥራት ይቻላል!

በምድር ላይ ሆኖ ዘለዓለማዊ ዋጋ ያለው ሥራ መሥራት ማለት ከዚህ አለም በስትያ ላለን ሕይወት አሁን በዚህ ምድር ሳለን የምናከማቸው መንፈሳዊ ስንቅ ማለት ነው። እግዚአብሔር ሰውን የፈጠረው ለጊዜያዊና ሥጋዊ ፍላጎቶች ማለትም ለመብላት፣ ለመጠጣት፣ ለመልበስና ለመዝናናት ብቻ አይደለም። እነዚህ ነገሮች በምድር ላይ ለመቆየት የሚያስፈልጉ መሣሪያዎች እንጂ የሕይወታችን ዋና ዓላማ አይደሉም፤ ይልቁንም የሰው ልጅ የተፈጠረው እግዚአብሔርን ለማወቅና ለማምለክ፣ በፍቅርና በቅድስና በመመላለስ ዘለዓለማዊ ፍሬ ለማፍራት፣ ሰዎችን ለማገልገል እና የተሰጠውን ጊዜና ሀብት ለበጎ ነገር የሚያውል መልካም መጋቢ ለመሆን ነው።

በምድር ላይ በሀብት ብንበለጽግ፣ ብዙ ቤቶችና ውድ መኪኖች ቢኖሩንም፣ ስንሞት ከእነዚህ ንብረቶች አንዱንም እንኳ ይዘን መሄድ እንደማንችል መረዳት ያስፈልጋል። ስለዚህ ምድር ጊዜያዊ መቆያና ወደፊት ወደ ዘለዓለማዊ ሕይወት የምንሸጋገርበት የመዘጋጃ ቦታ እንጂ የዘለዓለም መኖሪያችን አለመሆኗን ተገንዝቦ በጥንቃቄ መኖር አስፈላጊ ነው።

በመሆኑም ሰው በምድር ላይ ሲኖር ሚዛናዊ ሕይወትን መምራት ይኖርበታል። በምድር ላይ ለመኖር የሚያስፈልጉትን ነገሮች ለማሟላትና ምድራዊ ችግሮችን ለመፍታት እንደ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ያሉ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች የሰጣቸውን እውቀት በአገባብ በመጠቀም ጠንክሮ በመስራት እንዲሁም ደግሞ በዋናነትና በቀዳሚነት ግን ሙሉ ትኩረታችንን በእነዚህ ምድራዊና ቁሳዊ ነገሮች ላይ ብቻ ሳይሆን ዘለዓለማዊ ሕይወታችንን ማዕከል ባደረገ መልኩ ሚዛናችንን ጠብቀን ልንኖር ይገባናል። እግዚአብሔር ወደቅድስቲቱ ከተማ በሰላም ያግባን ተባረኩ።

✍️ Kibrayehu Yishak
https://t.me/compass_clcm
Telegram
Compass Life Coaching
🚨 JOIN OUR OFFICIAL GROUP: compasslifeclcm 🧭 Find your true north. ⚖️ Balance Spiritual & Secular Life to Truly Succeed. 📩 @kibrayehu
❤1👍1
September 2, 2026 33
በምድር ላይ ሆኖ ዘለዓለማዊ ዋጋ ያለውን ሥራ መሥራት ይቻላል! በምድር ላይ ሆኖ ዘለዓለማዊ ዋጋ ያለው ሥራ… — Joy online market — TG.ME