እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን። ሮሜ 8:28
"የእግዚአብሔር ኃይል ሺህ ዓለማትን የመፍጠርና በበረከት የመሙላት ብቃት አለው፤ ኃይሉ ተራሮችን እንደ ትቢያ ሊያደቅቅ፣ ባሕርን ሊያቃጥልና ሰማይን ሊያጠፋ ይችላል፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ኃይል በአማኙ ላይ ከቶ ፍቅር የጎደለውን ነገር አያደርግም። ክርስቲያን ሆይ! እግዚአብሔር ለገዛ ወገኖቹ ጨካኝ ወይም ክፉ ሊሆን እንደማይችል እርግጠኛ ሁን። እግዚአብሔር በበረከትና በምቾት ጊዜ እንደሚራራልህ ሁሉ፣ በመከራ ውስጥ እንድታልፍ ሲፈቅድም እንዲሁ ደግ ነው። ጥያቄው 'አንተ የእርሱ ልጅ ነህ ወይ?' የሚለው ብቻ ነው። ልጁ ከሆንክ፣ ተግሣጹ እንኳ የፍቅሩ መገለጫ ነው።"
ቻርለስ ስፐርጀን
10
1
1August 23, 2026 487 1