ቃቄ ውርድወት * <ሴት ልጅ ተመርጣ ብቻ ሳይሆን መርጣም ማግባት አለባት> 'ከዘመኗ የቀደመች' ስለሚባልላትና፤… — Joy online market — TG.ME

* ቃቄ ውርድወት *


<ሴት ልጅ ተመርጣ ብቻ ሳይሆን መርጣም ማግባት አለባት>


'ከዘመኗ የቀደመች' ስለሚባልላትና፤ በ1840ዎቹ ከጉራጌ ማሕበረሰብ ስለተገኘችው ቃቄ ውርድወት(ቃቄ የአባቷ ስም ሲሆን ውርድወት የእርሷ ስም ነው። በሀገራችን ከልጅ በፊት የአባት ስም በቅድሚያ የሚጠራበት ባሕል እንዳለ ያውቋል?)ምን ያህል ታውቃላችሁ?

ይህች ሴት በዘመኗ በጉራጌ ማሕበረሰብ ዘንድ 'ኧጆካ' እስከሚባለው ከፍተኛው ሸንጎ ድረስ ለሴቶች መብት የተሟገተች ትንታግ ነበረች። ዛሬ ላይ ቀለም ቆጥረዋል ከምንላቸው ከብዙዎቹ እንስቶች በተሻለ ስለ ሴቶች ክብር የቆመች አብዮተኛ እንስት ነበረች።

ለማናቸውም ስለዚህች ጀግና ሴት ታሪክ አጠር ያለ ማብራሪያ ከፈለጋችሁ እነሆ ሊንኩ https://t.me/AdissAdmas/32080

በተጨማሪም ሰፋ ያለ ማብራሪያ ለሚሻ የእንዳለ ጌታ ከበደን 'እምቢታ' መፅሀፍን እጋብዛለሁ።
Telegram
Addis Admass
ቃቄ ውርድወት ዛሬ ብታየን ምን ትል ይሆን? ቃቄ ውርድወትን አወቃችኋት? ቃቄ የጉራጌዋ ሴት? 'ወንዶች እንደፈለጉ ሶስትም አራትም ያገባሉ' የሚለውን ባህል 'እምቢ' ብላ የቆመችው? ከመቶ ዓመት በፊት? 'ወይ አንድ አግብቶ አርፎ ይኑር: ወይም እኔም እንደሱ የፈለግሁትን ያህል ባል ላግባ' ያለችው? 'ባህላችንን ልታበላሽ' ብለው ነበር የተቃወሟት:: 'ሴቶቻችንን እንደሷ ልታሳስብብን' ብለው…
❤3
August 14, 2026 1K 3