የጽንስ ምርመራና ሕክምና ማዕከል በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ተመርቆ ተከፈተ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም… — St.Paul's Hospital Millennium Medical College — TG.ME

የጽንስ ምርመራና ሕክምና ማዕከል በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ተመርቆ ተከፈተ

ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ የልህቀት ማዕከል በማድረግ ያቋቋመውን የጽንስ ምርመራና ሕክምና ማዕ ከል(Fetal Diagnostic & Intervention Center ) በዛሬው ቀን ተመርቆ በይፋ ተከፍቷል፡፡

በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የጤና ሚኒስትር ዴኤታዋ ክብርት ፍሬሕይወት አበበ እንደተናገሩት የእናቶችና ሕጻናት ሞትን ለመቀነስ እንዲህ ዓይነቱ ማእከላት ትልቅ ሚና አላቸው ብለዋል፡፡ ማእከሉ የእናቶችን ጤና በመጠበቅ ሕጻናት ከመወለዳቸው በፊት በማህጸን ውሰጥ እያሉ በቂ ክትትልና ህክምና በማድረግ ጤናማ ትውልድ ለመገንባት ያስችላል በማለት አስረድተዋል፡፡
ክብርት የጤና ሚኒስትር ዴኤታዋ ክብርት ሰኻረላ አብዱላሂ ማእከሉ መንግስት የጤና ቱሪዝምን ላይ በትኩረት ሰጥቶ አየሰራ እንደሚገኝ ገልጸው : ይህ ማዕከልም በዚህ ረገድ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ የጎላ ነው ብለዋል፡፡ ወደፊትም ሚኒስተር መስሪያ ቤታቸው በዚህ ረገድ ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል፡፡

የኮሌጁ ፕሮቮስት ዶር ሙሉቀን ተስፋዬ በበኩላቸው ኮሌጁ ለሕብረተሰቡ የሚሰጠው አገልግሎትምንግዜ የላቀ እንዲሆን ይሰራል ብለዋል፡፡ ይህ ማእከልም አንዱ ማሳያ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም ማእከሉ የሕክምና መስጫ ብቻ ሳይሆን ከሀገር ውስጥ እና ከተለያዩ አፍሪካ ሀገራት የሚመጡ ከፍተኛ ሐኪሞችንም ለማሰልጠን ያስችላል፡፡ በአሁኑ ወቅት ቁጥራችው ከሁለት መቶ በላይ አፍሪካውያን ተማሪዎች በኮሌጁ ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ ይገኛሉ በማለት ፕሮቮስቱ ገልጸዋል፡፡
ማዕከሉ የሕፃናትን የጤና ሁኔታ ከመወለዳቸው በፊት ( በማሕጸን እያሉ ) የጤና ችግራቸውን በመለየትና ተገቢውን ክትትልና ሕክምና ይሠጣል፡፡የሕክምናማእከሉ ዋና ተግባራት መካከል የፅንሱን የጤና ሁኔታ በቅድሚያ መመርመር፡የልብ፣ የአንጎል፣ የአከርካሪና ሌሎች የፅንስ እክሎችን መለየት፡የመቀንጨር ችግር ያለበትን ጽንስ መለየትና ማከም ፡በእርግዝና ወቅት በእናቱቱ ላይ እና በጽንሱ ላይ ከፍተኛ የጤና ስጋት ይሆናሉ የተባሉ በሽታዎችን ማከም ፡ መከታተልእና ማዳን፡የፅንሱን እድገትና አቀማመጥ በዝርዝር መከታተል፡እንደ ዳወን ሲንድሮም ያሉ የዘረመል ችግሮችንና በጽንስ ወቅት የታዩ አካላዊ ጉድለቶችን ከመወለዱ በፊት በመለየት፡ፅንሱ ገና በማህፀን ውስጥ እያለ ሕክምና በመስጠት ማከም እና ሌሎችም ተዛማጅ ሕክምና አገልግሎቶች እንደሚሰጥ በምረቃ ስነ ሥርዓት ወቅት ተገልጿል፡፡
ማዕከሉ ዘመናዊ የሕክምና መሣሪያዎችና በዘርፉ የሰለጠኑ ባለሙያዎች የተሟሉለት ነው፡፡
ማዕከሉ በዘመናዊ መሣሪያዎችና በሰው ኃይል አቅም በአገራችን ከፍተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ የፅንስ ምርመራና ሕክምና ማዕከል እንደሆነም ተገልጿል።
August 15, 2026 4.3K 1