ዜና ሣትኮም
በገጠርና በከተማ በታዳሽ ሃይል ዕቃዎች አቅርቦቱ በተደራሽነቱም ሰፊ አድማስ ያለው በኢንተር ኢትዮÉያ ሶሉዩሽን ከኦሮሚያ ክልል ከተለያዩ አካባቢዎች ለተመረጡ 15 ከፍተኛ ባለሙያዎች
Solar energy system Installation and Maintenance
ላይ በተቋማችን ለአንድ ሣምንት ያህል ሲሰጥ የቆየው የሶላር ኢነርጂ ሲስተም ዕቃዎች የጥገናና የኢንስታሌሽን ሥልጠና በተመደበው የጊዜ ሠሌዳና በሚፈለገው የጥራት ልክ ተሰጥቶ በተሣካ ሁኔታ መጠናቀቁና ሠልጣኞችም በድምቀት መመረቃቸው ተገለፀ::
ሥልጠናው ያካተታቸው Repair, Refurbishment, and Maintenance of Solar Home Systems (SHS), Productive Use Energy (PUE) Systems, Solar Refrigerators, Solar Water Pumps, Solar Fans, and Lithium-Ion Battery Technologies ላይ መሆኑ የተጠቀሰ ሲሆን
ከዚህም ጋር በተያያዘ ለሥልጠናው መሣካት ከፍተኛውን ድርሻ ለተወጣችሁ የተቋማችን መምህራንና ሠራተኞች* ወደር ለማይገኝለት የሥልጠና ዲስፕሊናችሁ ውድ ሠልጣኞቻችንም ምሥጋናዬ ይድረሳችሁ ሲል የተቋሙ አስተዳደር አስታውቋል::
በሌላም በኩል በከፍተኛ የውጪ ምንዛሬ ተገዝተው ወደ ሀገር የገቡ የሶላር ኢነርጂ ሲስተም ዕቃዎችን የአገልግሎት ዘመናቸውን ለማስቀጠል ተግቶ ከሚሰራው ኢንተር ሶሉዩሽን ጋር በመተባበር ብቁና ተመራጭ ባለሙያዎችንም ለማፍራት የሁል ጊዜ ጥረትና ዓላማችንን ማስቀጠል ተቀዳሚ ግባችን መሆኑንም እናረጋግጣለን በድጋሚም ቃላችን እናድሣለን ሲል የተቋሙ አስተዳደሩ በዚህ አጋጣሚ አስተውሷል::
ሣትኮም የምርጥ ባለሙያዎች መፍለቂያ!
18
11
2June 30, 2026 5.3K 7






