ቦክስ ጊታር እየተጫወታችሁ የምትዘምሩ ዘማሪዎች እነዚህን ነገሮች ማድረግ የለባችሁም።
(ለሚመለከታቸው ላኩላቸው)
1. ከሙዚቀኞች ጋር ሳይለማመዱ መዘመር:
ይሄ በጣም የተሳሳተ ልማድ የሚሆንበት ምክንያት ከሙዚቀኞች ጋር ሳትለማመዱ መድረክ ላይ ስትቆሙ የምትጫወቷቸው ኮርዶች ሙዚቀኞች ከሚጫወትቷቸው ኮርዶች ጋር ስለሚምታታ ለጆሮ የሚከብድ ይሆናል። አብራችሁ ተለማምዳችሁ ኮርዶቹን እና ሜሎዲዎቹን ተመሳሳይና አብረው የሚሄዱ ካለደረጋችኋቸው የሙዚቀኞቹ ማጀብ ምንም ዋጋ ስለሌለው ለብቻችሁ ወይም ምት(እንደ ኮንጋ እና ማራካ አይነት አኩስቲክ የምት መሳሪያዎች ካሉ በእነሱ በመጠቀም) ብቻ የሚቻወትላችሁ ሰው ካለ በሱ ብቻ ታጅባችሁ ብትዘምሩ የተሻለ ነው።
ይህ የተሳሳተ ልማድ ከሞላ ጎደል በሁሉ በጊታር በሚዘምሩ ዘማሪዎች ላይ የሚታይ ነው። ሊቀር ይገባል።
2. ሳትለማመዱ ብትቀሩ እንኳን ኮርድ ፕሮግሬሽኑን ለሙዚቀኞች ሳትነግሩ በመሰላቸው መንገድ እንዲጫወቱ መተው:
ይሄም ሌላው የተሳሳተ ልማድ የሚሆንበት ምክንያት ሁለታችሁም(ሙዚቀኞች እና ዘማሪው) በራሳችሁ መንገድ ትጫወታላችሁ። ይህ ደግሞ አንድ ላይ የምትጫወቱት ሙዚቃ ልክ እንደ ዘይት እና እንደ ውሃ ያልተዋሃደ እንዲሆን፣ ለጆሮም ምንም ስሜት የማይሰጥ እንዲሆን ያደርገዋል።
3. የግድ አስፈላጊ ሆኖ ካልተገኘ በስተቀር እና ካልተለማመዳችሁ በስተቀር በፈጣን(Groovy) ምቶች ማለትም እንደ ሬጌ፣ክችክችካ፣ወሎ ቢት፣ ዲስኮ ወዘተ ምቶች ላይ ቦክስ ጊታር መጫወት የለባችሁም። እደግመዋለሁ የለባችሁም! ይሄ ልማድ ሙዚቃው በጣም አስቀያሚ እንዲሆን ያደርገዋል።
እነዚህንም ለማድረግ ፈቃደኛ ካልሆናችሁ ጊታር እየተጫወታችሁ መዘመር ትታችሁ እንደሌላው ዘማሪ በባዶ ዘምሩ። በጊታር መዘመር ግዴታ አይደለም አይደል?
