Reshad (ረሻድ): post #1505 — TG.ME

ጎግል ከ1.75 ሚሊዮን በላይ የፖሊሲ ጥሰት የፈጸሙ አደገኛ መተግበሪያዎችን ከፕሌይ ስቶር አገደ

ጎግል እ.ኤ.አ. በ2025 ባደረገው የደህንነት ግምገማ፤ የተጠቃሚዎችን መረጃ ያለአግባብ ለመውሰድ የሞከሩና የፖሊሲ ጥሰት የፈጸሙ ከ1.75 ሚሊዮን በላይ መተግበሪያዎችን ከፕሌይ ስቶር (Google Play) ማስወገዱን አስታውቋል።

ከእነዚህ መተግበሪያዎች መካከል ከ255,000 በላይ የሚሆኑት የግል መረጃዎችን ለመስረቅ በመሞከራቸው የታገዱ መሆናቸውን ኩባንያው ገልጿል።

ጎግል አደገኛ መተግበሪያዎችን በፍጥነት ለመለየት የሰው ሰራሽ አስተዝህሮ (Generative AI) ቴክኖሎጂን መጠቀም መጀመሩን በዚሁ ሪፖርቱ ያመለከተ ሲሆን፤ ከኦፊሴላዊው የፕሌይ ስቶር ውጭ የወረዱ (Sideloaded) 27 ሚሊዮን አደገኛ መተግበሪያዎች (Malicious Apps) በጎግል የደህንነት ሲስተም መለየታቸውንም ይፋ አድርጓል።

ከአደገኛ ሶፍትዌሮች ራሳችንን ለመጠበቅ ምን እናድርግ?

👉ታማኝ ምንጮችን ብቻ ይጠቀሙ፦ መተግበሪያዎችን ከታወቁና ይፋዊ ከሆኑ የ-App Store መድረኮች ብቻ ይጫኑ።

👉የመተግበሪያ ፈቃዶችን (Permissions) ይፈትሹ፦ አንድ መተግበሪያ ከሚሰጠው አገልግሎት ውጭ የግል መረጃዎችን (እንደ ካሜራ፣ ስልክ ቁጥሮች ወይም ጋለሪ) እንዲያገኝ ሲጠይቅ በጥንቃቄ ይመርምሩ።

👉የስልክዎን ሶፍትዌር ያዘምኑ፦ እንደ "አንድሮይድ 16" ያሉ አዳዲስ ኦፐሬቲንግ ሲስተሞች የላቀ የደህንነት ጥበቃ ስለሚሰጡ ስልክዎን ሁልጊዜ በማዘመን (Update በማድረግ) ይጠቀሙ።

@reshadapp
        @reshadapp
👍4
February 25, 2026 791